የግልፅ ያጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክ/ከተማ የቀይ ኮከብ አፀደ ህፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት በ2013 ዓ.ም በጀት
- አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- አላቂ የህክምና እቃዎች፣
- የላብራቶሪ እቃዎች፣
- የመደበኛና የቅደመ መደበኛ ህፃናት ሰርተፍኬት፣
- አላቂ የጽዳት እቃዎች ፣
- የንፅህና መጠበቂያ ማስከ፣ ጓንትና ሳኒታይዘር፣ቋሚ እቃዎች ፤
- የደንብ ልብስ እና ስፌትን ጨምሮ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የምትፈልገተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትወዳደሩ ት/ቤቱ ይጋብዛል፡፡
- በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑንና የቫት ተመዝጋቢ መሆንዎትን የሚገልፅ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በቀይ ኮከብ አፀደ ህፃናትና የመጀ/ደ/ትቤት በመቅረብ መውሰድ የሚችሉና የመወዳደሪያ ለነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቢሮ ቁ 30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 2000(ሁለት ሺ) በሲፒኦ ወይም በካሽ ከማረጋገጫ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ጨረታው በ11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀይ ኮከብ አፀደ ህፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁ. 30 ይከፈታል፡፡
– ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ቀይ ኮከብ አፀደ ህፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት ልዩ ስሙ ጣሊያን ሰፈር ወይም ከዮሃንስ ቤተክርስቲያን ወደ ጎጃም በረዳ በሚወስደው መንገድ አራት መንታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በት/ቤቱ ስልክ ቁጥር 011-1-11-56-03 ደውለው ይጠይቁ ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
በአራዳ ክፍለ ከተማ የቀይ ኮከብ አፀደ
ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት