ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2013 ዓ.ም ለሰራተኞች የሚውል
- ብትን ጨርቅ፣ ሸሚዝ፣ ካፖርት፣ የዝናብ ልብስ፣ ጫማ ፣
- የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ፣
- የሲኖትራክና የቲዮታ መኪና ጎማና ከለማዳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ፦
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ቲን ነምበር ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና መረጃ ኦርጅናል የማይመለስ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አይዘው መቅረብ አለባቸው፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የንግድ ፈቃድ ያላችሁ መሆን አለባችሁ
- ተጫራቾች የምታቀርቡት ዋጋ ከ 200,000.00 ( ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ) ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ቢሮ ቁጥር 3 በመሄድ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጨረሻ ሰነዶቻቸው ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 10/02/2013 ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ከጠቅላላ ዋጋ 2 % ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን እቃ ናሙና በጨረታው እለት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች በጨረታው ተሳታፊ አይሆንም፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች የሚጫረትበትን አልባሳት፣ የመኪና ጎማ፣ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ በሰነዱ መሰረት ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በፖስታው ላይ የተወዳደረበት አልባሳት አይነት ከላይ መጻፍ አለበት
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ሲታወቅ የጠቅላላ ዋጋውን 10 % የውል ማስከበሪያ በመያዝ ውል በመውሰድ ወደ ስራ መግባት ይኖርበታል
- ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፈርማ መኖር አለበት ስርዝ ድልዝ ካለ በፊርማ መረጋገጥ አለበት ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ
ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ