Development and Web Design / ICT / Networking Equipment and Installation / Software Provision

በአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለ100 Workstation ለ8 Server በድምሩ ለ108 ኮምፒዩተሮች Licensed የሆነ Antivirus ከተፈቀደላቸው ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

አገልግሎት ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 

በድጋሚ የወጣ Anti-Virus ግልፅ ጨረታ ቁጥር AWWCE NCB Main 16/2012 

በአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለ100 workstation ለ8 server በድምሩ ለ108 ኮምፒዩተሮች Licensed የሆነ Antivirus ከተፈቀደላቸው ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያሟሉ ድርጅቶችን በጨረታው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ 

 1.  ተወዳዳሪዎች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 2. ተጫራቾች የተጠየቁት Anti-Virus ግዥ የሚሸጡበትን ዋጋ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ስርዝ ድልዝ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከተገኘ አጭር ፊርማ መኖር አለበት አጭር ፊርማ ከሌለ ግን ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
 3. የሚቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ሕጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም፣ ፊርማና ማህተም መኖር አለበት ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡ 
 4. ሌሎች ከስራው ጋር የተያያዙ ማንኛውም ወጪዎች ታክስን ጨምሮ በተሰጠው ዋጋ ላይ ተጠቃሎ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 5. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮእስከ 20(ሃያ)ተከታታይቀናትባህርዳርከተማቀበሌ14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮአችን 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ ወይም በድርጅታችን የባንክ አካውንት ቁጥር 1000265163223 የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል የከፍያ ማረጋገጫውን ማስረጃ ይዞ በማቅረብ ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 በሚገኘው የድርጅቱ ህንፃ 3ኛ ፎቅ በመምጣት ሙግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ከቀኑ 8፡ 00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 
 6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 10,000.00 / አስር ሺህ ብር  ያለቅድመ ሁኔታ ሲጠየቅ ለገዥ የሚከፈል ጋራንቲ ወይም CPO ድርጅታችን በአማራ ውሃ ሥራዎች ድርጅት ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡ 
 7. ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒካል ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ፤ የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ (ፋይናንሻል ሰነድ) በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል የጨረታ ማስከበሪያው እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ (ይናንሻል ሰነድ) ጋር ኦርጂናል ሲፒኦ / CPO | በማያያዝ በአንድ ፖስታ እንዲሁም የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት CPO ኮፒ በማያያዝ በኣንድ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የሥራ ቀናት ውስጥ አማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮ አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
 8. . በቴክኒከ ግምገማው ያላለፈ ድርጅት የፋይናንስ ሰነዳቸው እንደታሸገ ይመለሳል፡፡
 9. ውድድሩ የሚካሄደው በቴክኒከ ያለፉ ድርጅቶች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ በጥቅል የሰጠው ድርጅት አሸናፊ ይሆናል፡፡
 10. አሸናፊው ድርጅትስራውን ጨርሶ Anti-Virus ጭኖ የሚያስረክብበትን ጊዜ ውሉ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ30 ሰላሳ/ ቀናት መሆን ይጠበቅበታል፡፡
 11. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10%በሲፒኦ /CPO/ በድርጅቱ ስም በማስያዝ ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡ የውል ማስከበሪያ ያላስያዘ እንደሆነ ድርጅቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው፡፡ የደረሰው ጉዳት ከውል ማስረከቢያው በላይ ከሆነ ድርጅቱ ልዩነቱን በህግ ከአቅራቢው መጠየቅ ይችላል፡፡ 
 12. Antivirus ዥው በሚፈፀመው ውል መሠረት ያላቀረበ አሸናፊ አቅራቢ ለዘገየበት አገልግሎት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 0.1% በየቀኑ መቀጫ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ይህ ሙቀጫ ከጠቅላላ ዋጋው 10% ሊበልጥ አይችልም፡፡ ነገር ግን የቅጣት ጠቅላላ ዋጋው ከ 10% ከበለጠ ገዥ ለሻጭ ማሳወቅሳይገደድ ውሉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰ መብት አለው:: 
 13. ድርጅቱ፡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: 

ስልክ ቁጥር፡- 058222-1479 ወይም 058226-5203 ፋከስ ቁጥር፡- 058222-1335 

የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ባህር ዳር