ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሀ/ማ/ከ/ወ ገ/ኢ/ት/ ፅ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ለ2012 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- 1. የስፖርት ቁሳቁስና መገልገያ፣
- 2. የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ ቁሳቁሶች፣
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TiN/ ያላቸው እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በአቅራቢነት ማስረጃ ያላቸው
- የግዥው መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ MAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርነት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50/ሀምሳ ብር/ ብቻ በመከፈል ከግዥ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሀ/ማ/ከ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ /ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል ፡፡16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቹ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው እስከሚዘጋበት እስከ 16ተኛው ቀን 3፡30 ድረስ ናሙና ማቅረብ መቻል አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን እንዳዋጭነቱ በተናጠል ወይም በጥቅል ሊሰጥ ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0116190146/148 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ 130 ኪሜ ርቀት ወደ ደብረብርሃን 80 ኪሜ ርቀት በሚወስደው አስፋልት ከሸኖ ከተማ አለፍ ብሎ ወደ ምስራቅ 39 ኪሜ ገባ ብሎ እንገኛለን፡፡
የሀ/ማ/ከ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
ሾላ ገበያ