ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ግ.ጨ ቁጥር ወ.ሶ.ዩ፤ – 07/13
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2013 በጀት ዓመት የተማሪዎች ካፍቴሪያ ጠረጴዛዎች እና ወንበሮች በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የዕቃዎች ዝርዝር የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን
- የተማሪዎች ካፊቴሪያ ጠረጴዛዎችና ወንበሮች በድጋሚ የወጣ—- ብር 200,000.00
በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡
- በሚወዳደርበት ዘርፍ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ፣ የግብር ከፋይ መለያ TIN ሰርተፊኬት፣ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፊ ደብዳቤና የድረ–ገጽ ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ (CPO) ፣ የባንክ ጋራንቲ ወይም ጥሬ ገንዘብ ከላይ የተጠየቀውን ገንዘብ መጠን በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የንግድ ዘርፍ ያላቸዉን ሰነዶች ኮፒዉንና እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዉ ባዘጋጀው ጨረታ ሠነድ ላይ በሚነበብ ጽሑፍ ዋጋውን በመሙላት የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ጨረታ ሠነዶችን የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለ ጊዜ ውስጥ ከዩኒቨርሲቲው ዋናዉ ግቢ በአስተዳደር ሕንፃ 1ኛዉ ፎቅ ከጨረታ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ እና አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ ለሠነዱ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በኢት/ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000018182789 በወላይታ ሶዶ ዩነቨርሲቲው ስም በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ በ15ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በአስተዳደር ሕንፃ በ1ኛ ፎቅ ላይ ግዥ ዳሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በእለቱ ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በአስተዳደር ሕንፃ በ1ኛ ፎቅ ላይ ግዥ ዳሬከቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- 15ኛው ቀን የሚውለው ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ ጨረታዉ የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው ሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሠዓት መሠረት ይሆናል፡፡
- ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ውል ከፈረመ በኋላ ለተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘት ዋስትና ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 046551-46-15 ወይም 09110155445 ፋክስ 0465515113፡፡
ማሳሰቢያ፡– የጨረታ ሠነዱን ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ፡፡
- አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ ስልክ ቁጥር፡– 0913790195/0912881430
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ