ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን በቆቦ ከተማ አስተዳደር ትም/ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቆቦ አጠ/ከፍ/መሰ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2013 ዓ/ም በተያዘው በጀት ዓመት የአስተዳደር ህንፃ ግንባታ ኩንታራክተሮችን በጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት/ማስገባት/ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናቶች ማለትም ከ23/02/2013 ዓ/ም እስከ 13/03/2013 ዓ/ም ድረስ የምትጫረቱ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ ዋጋ መሙላያ ዝርዝር ከት/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ 100 ብር ገዝቶ በመውሰድ ሞልቶ በስም በታሸገ ፖስታ ለት/ቤቱ በማስገባት የምትጫረቱ መሆኑን እያሣወቅን፡፡
ጨረታው የሚከፈተው በ21ኛው ቀን 13/03/2013 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ በ22ኛው ቀን 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ቀን የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
የጨረታ አይነት የአስተዳደር ህንፃ ግንባታ የተጫራቾች መመሪያ
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ስራ ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
- የምዝገባ ሰርተፊኬት/ቲን/ ያላቸው፣
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋ መሆን አለባቸው፡፡
- የግምባታ ፈቃዳቸው ከደረጃ 9 እና በላይ ያሉትን ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች የዋስትና ማስከበሪያ 10 በመቶ እና የቅድሚያ ክፍያ ማስከበሪያ 30 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ዋጋው ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖረው በጥንቃቄ መሞላት አለበት፡፡
- የሚሰሩ የግንባታ ስራ ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከዋጋ ማቅረቢያው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ሙሉ በሙሉ የግንባታ ወጭውን በራሱ ወጭ አጠናቆ በመስራት ማስረከብ የሚችል፡፡
ማሣሰቢያ፡- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልየመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች እኩል ከወጡ አሸናፊውን በድርድር የሚለይ ይሆናል፡፡
የበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0920315258 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
የቆቦ ከተማ አስተዳደር ትም/ት/ጽ/ቤት