ግልጽ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ የክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት ለ2013 በጀት አመት በመደበኛ በጀት
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያና ተያያዥ እቃዎች ግዥ፣
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች ግዥ፣
- ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስና ተያያዥ ዕቃዎች ግዥ፣
- ሎት 4 የሠራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ እና
- ሎት 5 የህንጻና ተያያዥ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መገለጫው ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 50/ አምሳ ብቻ በመክፈል ግልጽ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከውጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ግራውንድ ላይ ቢሮ ቁጥር 48 ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚያቀርቡትን ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚፈልጉ ለጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመክፈል ደረሰኙን ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በክልል ም/ቤት ጽ/ቤት በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ስዓት እስከ 16ኛው ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሪክትሮሪት በግዥ ቢሮ ቁጥር 40 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን ከመክፈቱም በተጨማሪ ጨረታው ሲከፈት ለሚተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 40 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582264722 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0582262151 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የአማራ ብሔራዊ የክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት