ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለ2013 የበጀት አመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የአላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች እንዲሁም የአገልግሎት ጥቅል ግዥ፡-
- ሎት 1 የመኪና ጎማ ከነካላማዳሪው
- ሎት 2 የኘላስቲክ ኮርኒስ ለ1 ካሬ የእጅ ዋጋ
- ሎት 3 የመ/ቤቱ ዐቃብያን ህግና ሰራተኞች መታወቂያ በማይካ /water Proof/
- ሎት 4 የመ/ቤቱ አጠቃላይ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አመታዊ ጥገና የእጅ ዋጋ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- . የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- . የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ብር 200 ሺህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 30 ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይቻላል፡
- . ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መ/ቤት ከግዥና ፋይ/ንብ/ አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለትም ከ28/2013 እስከ 12/2013 ዓ/ም 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን 13/04/12 ዓ.ም 3፡00 ተዘግቶ በ3፡30 ይከፈታል፡፡ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582263100/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መ/ቤት