የአሳ መኖ የሳር ማሰሪያ ቤለርና የዶሮ
ማጓጓዣ ሳጥን ግዥ የብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀከት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለባህር ዳር አሳና ሌሎች የውሀ ወስጥ ህይወት ምርምር ማዕከልና ለአንዳሳ እንስሳት ምርምር ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ በግዥው መለያ ቁጥር ET-AMH-LFSDP-GORFB-03/2020 (ሎት 01) የተመጣጠነ የአሳ መኖ (ተንሳፋፊ የሆነ) እና በግዥው መለያ ቁጥር ET-AMH-LFSDP GO-RFB-04/2020 (ሎት 02) የሳር ማሰሪያ ቤለርና የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (ኩብ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተለትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ከላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከፋይናንሻል ፕሮፖዛል ከኦሪጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል አብከመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀከት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 01 (የአሳ መኖ) ብር 8,000.00 (ስምንት ሺህ ብር) ላሎት 02 (የሳር ማሰሪያ ቤለርና የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን) ብር 20,000, 00 (ሀያ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን የቴከኒክ ዶክመንትና የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ዶከመንት) ዋናና ቅጅ በማለት በፖስ አሽጎ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀከት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማቅረብ ይችላል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባባሪያ ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር- 0583205297 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት
ፕሮጀከት