የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግብ/4330/13
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የግብርና ግብአቶችና ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት በድን ለ2013/2014 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል 1,640,000 አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ሺህ ) ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ በዞናችን ባሉ 3 ዮኒየኖች በስራቸው ስሚገኙ 247 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባለው 6 ወር ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። ስለዚህ በሥራው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማኅበር/ኢማ፤ በአዲሱ አደረጃጀት የብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ አጓጓዦች የማጓጓዣ ታሪፋችንን በማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መሠረት በታሸገ ፖስታ በማቅረብ በጨረታ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
በዚህም መሰረት፡–
- ሎት -1 ጎዛምን ዩኒየን የደብረማርቆስ ማዕከላዊ መጋዘኖች በስሩ ባሉ መሰረታዊ ማህበራት /መጋዘን
- ሎት 2- ሞጣ ዩኒየን፣ ሞጣ ከተማ፣ ከግንደ ይን፣ ቀራንዮ እና ለማሪያም፣ ማዕላዊ መጋዘኖች በስሩ ባሉ መሰረታዊ ማህበራት መጋዘን
- ሎት 3-ግዮን ዩኒየን ፣ ደጀን ማዕካላዊ መጋዘን በስሩ ባሉ መሰረታዊ ማህበራት መጋዘን ሲሆን፤
ተጫራቾች ማሟላት ያለባችው ግዴታዎች ፡-
- የንግድ ሚኒስቴር ወይም ቢሮ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ የመንግስት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል::
- የገቢዎችና ግምሩክ ባለስልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም ቲን ነምበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- በጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- እንዲህም ተጫራቾች የሚያቀርበት ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- የተሽከርካሪ ዝርዝር /ተ.ቁ፣ የሰሌዳ ቁጥር፡ የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም/ የሚያስረዳ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2013 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- እቃውን አጠቃሎ የሚያስረክብበትን ቀን እና ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበትን ቀን መጥቀስ የአለበት ሲሆን ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበትንና የሚያስረከብበትን ቀን ካልገለጸ ከ ገፅ 10 እስከ ገፅ11 የመገምገሚያ መስፈርት በሚለው ርዕስ ስር ከተራ ቁጥር 1 እስከ1 4 በሰነዱ ላይ በተገለጸው መንገድ ለማቅረብ እንደተስማማ ይቆጠራል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፡ የመጠን ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ዩኒየን የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ምስ/ጎጃም ዞን ገ/ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ ማለትም ለሎት 1(ኣንድ) ብር 489,714.00 (አራት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ አስራ አራት) ለሎት 2 (ሁለት) ብር 250,607,00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሽህ ስድስት መቶ ሰባት) ለሎት 3. ብር 303,285,000 (ሶስት መቶ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሚወዳደሩበት ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ በግብርና ግብአትና ገጠር ፋይናንስ አቅ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም 3/3/2013ዓ.ም 4፡00 ሰአት ድረስ ነው፡፡ልከ 4 ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ሣጥኑ ይታሽጋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ማለትም በ3/3/2013 ዓ.ም በ4:30 /አራት ሰዓት ተኩል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- አንድ ተጫራች በአንድ ዩኒየን ውስጥ ከተዘረዘሩት ማኅበራት መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም ከውድድር ውጭ ያስደርጋል።
- መሥሪያ ቤቱ የሚያወዳድረው ለአንድ መሠረታዊ ማህበር ለኣንድ ኩንታል በሚያቀርበው ነጠላ ዋጋ ነው፡፡
- የግብርና መምሪያው የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0587716828 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ
ደ/ማርቆስ