Cleaning and Janitorial Equipment and Service / Service / Transportation Service / Vehicle

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2013 በጀት አመት የፅዳት አገልግሎት /outsource/ : የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 1/2013 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2013 በጀት አመት

 • ሎት1. የፅዳት አገልግሎት /outsource/
 • ሎት2 የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከሀምሌ 1/2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

በዚህም መሰረት፡

 1.  በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ 
 2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TገN/ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ 
 3. የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ 
 4. የጨረታ ሰነዱን ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 62 መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
 5. የጨረታ ማስከበሪያ ያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ያክሉን ለሆስፒታሉ በCPO /በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ አለባቸው። 
 6. ከብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ በላይ ለሚገዙ አገልግሎቶች 2%የመቁረጥ ግዴታ አለብዎት። 
 7. አሸናፊ ሆኖ የሚገባው ተጫራች ለሆስፒታሉ የፅዳት አገልግሎቱን ለ24 ሰዓት ሳይቆራረጥ መስጠት አለበት። በመሆኑም የፅዳት ቋሚና አላቂ ግብዓቶች በወሩ መጀመሪያ ከ1-3 ባሉት ቀናት ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡ 
 8. ቋሚ እቃዎች መጀመሪያ ሙሉ ለሙሉ ከገቡ በኋላ ሲሰበሩ፣ ሲበላሹ፣ ሲያልቁና ለስራ አመቺ በማይሆኑበት ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል ማቅረብ አለባቸው፡፡
 9. ተሽከርካሪው በወንበር 24 /ሀያ አራት ሰው የመጫን አቅም ያለው፡፡ 
 10. የተሽከርካሪው የስሪት ዘመን እንደ ኤውሮፓ አቆጣጠር 2010 እና ከዚህ ወዲህ የተመረተ፡፡ 
 11. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ለመኪናዉ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ወጪዎችን እና የናፍጣ ክፍያ በራሱ የሚሸፈን መሆኑን ታሳቢ አድርጎ ይሆናል፡፡
 12. ተሽከርካሪው ሙሉ ቀን ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚሰጥ በመስጠት የሚችል መሆን አለበት፣ 
 13. የተሽከርካሪው ሊብሬ በተጫራቹ ስም የሆነ፣ኢንሹራንስ እና ሶስተኛ ወገን የተገባለት እንዲሁም የቴክኒክ ምርመራ /ቦሎ/ ያሰራ መሆን አለበት፡፡
 14. ተሽከርካሪው በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የተመዘገበ መሆን ያለበት ሲሆን ለሁለቱም ሎቶች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
 15. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በCPO /በጥሬ ገንዘብ/ በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን ይኖርበታ። 
 16. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ዝርዝር አባሪ ዶክሜንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 
 17. ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡ 
 18.  ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሆስፒታሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቶች ባይገኙም የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
 19. ለሁለቱም ሎቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋ መሙያ ላይ ማየት ይቻላል፡፡ 
 20. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ/ ዝግ ከሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀናት ይከፈታል፡፡
 21. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 22. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0925402088 ወይም 0914465336 ደውለው ይጠይቁ፡፡ 

አድራሻ፡ 

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ 190 ኪ

 

ሜትር ደብረሲና ከተማ 

በአብክመ ጤና ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር ጤና መምሪያeደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል