Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others / Vehicle / Water Engineering Machinery and Equipment

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የኮምቦልቻ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት የኮንስትራከሽን ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪ መሳሪያዎችን አከራይ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመከራየት ስራውን ማሰራት (አገልግሎት)ማግኘት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስተዳድርዞን በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የኮምቦልቻ ከተማ መንገዶችባለሥልጣን መ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ከፈዴራል መንገድፈንድ የበጀት ድጋፍ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ የከተማቀበሌ እና በተለያዩ የገጠር ቀበሌ የጠጠር መንገድ ከፈታና እዲስ የጠጠር ግንባታ ሥራ ለመሥራት እና በከተማ አስተዳደር ከውስጥ ገቢ በጀት ለሚያሠራው የጠጠር መንገድ ጥገናና ግንባታ ሥራ ሰሌክት ማቴሪያል ለማምረት ለመጫን እና ለማጓጓዝ ውሃ ለማርከፍከፍ መሬት ለማስተካከል እና የተቆረጠ አፈር ካርታዌ ለመጫን እና ለማጓጓዝ የሚያገለግል ገልባጭ መኪና ከነሎደሩ ፣ሻወር ትራከ መኪና የውሃ ቦቴ/ ግሬደር ፣ ዶዘር እና ኤክስካቫተር ባካፋ ኤክስካቫተር ከነጃከ ሃመሩ ማሽኖችንና ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ የሚችል የኮንስትራከሽን ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪመሳሪያዎችን አከራይ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽጨረታ አወዳድሮ በመከራየት ስራውን ማሰራት (አገልግሎት)ማግኘት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ መ/ቤቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላማንኛውም ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪ አከራይ ድርጅትበጨረታው መሳተፍ የሚችል መሆኑን ይገልጻል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
 2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ከገቢዎች የተጻፈ ማስረጃማቅረብ የሚችሉ፣
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TN NO.) ያላቸው፣
 4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀትየተሰጣቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብየሚችሉ፣
 5. ከላይ ተ.ቁ. 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውንማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘውበታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን የቴክኒካልና ፋይናንሻልፖስታዎች ለየብቻቸው በፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
 7. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሠነዱ ከተከፈተበትቀን ጀምሮ ለ 45 ቀናት ሲሆን፣ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያዋስትና (Bid bond) ለሚወዳደሩበት የጠቅላላውን ዋጋ 2%በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ለ 65 ቀን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮመቅረብ አለበት፡፡
 8. ለማሽነሪዎች (ለሎደር፣ ለውሃ ቦቴ፣ግሬደር፣ ዶዘር ኤክስካቫተርእና ገልባጭ መኪናዎች) የሚያስፈልጉ ነዳጅ፣ዘይት፣ግሪስ፣የጥበቃና ሌሎች ወጭዎች እንዲሁም ዶዘር ከአንዱ ቀበሌ ወደሌላ ቀበሌ ሰሌክት ማቴሪያል ለማምረት እና የመሬት ቆረጣ ስራለመስራት በሚጓጓዝበት ወቅት የሎቤድ ወጭ በአቅራቢያውድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡ የውሃ ቦቴ ፣ የገልባጭ መኪናከነሎደሩ፣ግሬደር፣ኤክስካቫተርእናዶዘር ዝርዝርእሰፔስፊኬሽንከጨረታ ስነዱ ላይ ያገኙታል፡፡
 9. ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድበሚጠይቀው ዋጋ አሞላል ብቻ መሞላት አለበት በሚጠይቀውዋጋ ኣሞላል ካልሞሉ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል፡፡
 10. አሸናፊው የሚለየው ፡የገልባጭ መኪና ከነሎደሩ ፣ የውሃቦቴ፣ ኤክስካቫተር፣ ዶዘር እና ግሬደር ማሽን በሎት ዋጋ ድምርይሆናል፡፡ነገር ግን ስራው የሚሰራው የተለያየ የበጀት ኮድ ስለሆነእያንዳንዱ ሎት ከምህንድስና ግምት በላይ ከሆነ ውድቅ ይሆናልስለዚህ ተጫራቹ ለእያንዳንዱ ሎት ተመጣጣኝ የሆነና ተገቢየሆነ ዋጋ ግምት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 11. ተጫራቶች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 7/2/2013-21/2/2013 ዓ.ም 11፡30 በኮምቦልቻ ከተማመንገድ ባለስልጣን ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 130በመቅረብ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሠነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
 12. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ዝርዝር ሰነድ የነጠላና ጠቅላላ ዋጋውንበመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናሉንና ሁለትኮፒ በመለያየትና በማሸግ በፖስታው ላይ የተጫራቹን ሥምናአድራሻ ለይቶ በመፃፍ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታሳጥን በ22/2/2013 ዓ.ም ከቀኑ እሰከ 4፡00 ሰዓት ኮምቦልቻከተማ መንገድ ባለስልጣን መ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደትቢሮ ማስገባት አለባቸው፡፡
 13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትበ22/2/2013ዓ.ም ዓ/ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያውእለት ከቀኑ 4፡30 ላይ በኮምቦልቻ ከተማ መንገድ ባለስልጣንመ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ ነገርግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ እና የሰዓልቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈትመሆኑን እንገልፃለን፡፡
 14.  መ/ቤቱ በማንኛውም መንገድ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉበሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::ለበለጠ መረጃ በኮምቦልቻ ከተማ መንገድ ባለስልጣን መ/ቤት ስቁ033 851 41 07 መጠየቅ ይቻላል፡
 15. .አወዛጋቢ የሆነ የቁጥርና የሂሳብ ስሌት አሞላል የሞላ ተጫራችየጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡
 16. .መስሪያ ቤቱ ካቀረበው የጨረታ ሰነድ አሞላል ውጭ የሞላተጫራች የጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- የመ/ቤቱ አድራሻ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህንጻአምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 130 ላይ ነው፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞንበኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር

ኮምቦልቻ ከተማ መንገዶችባለሥልጣን መ/ቤት