ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወ/ትም/ዋ/ጽ/ቤት ቆርቆሮ በግልጽ ጨታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቶች በጨረታው በመሳተፍ ከላይ በተቁ ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 /ሰላሳ ብር ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ይቻላል፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ እና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ስሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ /ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- እሸናፊ የሚለየው በየሎት ወይም ሰጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች 13/9/2012 ዓ.ም እስከ 27/9/2012 ዓ.ም በበየዳ ወረዳ ገ/ኢ/ልት ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰአት እስከ 11፡30 በመምጣት ማግኘት ትችላላችሁ የጨረታ ሳጥኑን 28/9/2012 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ህጋዊ ተጫራቶች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታ አሸናፊው ያሸነፈውን ንብረት በወረዳው ውስጥ በሚገኝ የንብረት መጋዘን አምጥቶ ማስረከብ የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታ አሸናፊው የትራንስፖርትም ሆነ ማውረጃ መጫኛ እና ማንኛውም ወጪ በራሱ አምጥቶ ማስረከብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሠረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቶች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0583272054 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ
የገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት