የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን በማቻከል ወረዳ በአማ/ቴ/ሙ/ማሰ/ኮሌጅ ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ
- ሎት 2 የህንጻ መሣሪያ
- ሎት 3 የእንስሣት ማቴሪያል
- ሎት 4 የመኪና ዕቃ
- ሎት 5 የልብስ ስፊት ዕቃ
- ሎት 6 የህክምና ዕቃ
- ሎት 7 የኤሌክትሪክ ዕቃ
- ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስዕቃ
- ሎት 9 የእጽዋት ዕቃ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ዕቃዎች በሰነዱ ላይ ይገኛሉ ስለሆነም ከዚህ
በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል::
- በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁTir /ቲን/ ያላቸው::
- . የግዥ መጠን ብር 200‚000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁTir 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- የሚገዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሣ ብር/ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ክፍል ገ/ያዥ ቢሮ ቁTir 4 ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ እና በላይ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአማ/ቴ/ሙ/ማ/ ኮሌጅ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ግዥ ባለሙያ ቢሮ ቁTir 9 በጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይኖርበታል::
- የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ3፡30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በዚያው እለት 4፡00 ይከፈታል፣
- ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፣
- የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል፣
- . የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የሚለየው በሎት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ነው፣
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉበትን ዕቃዎች አማ/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ድረስ በማምጣት ማስረከብይኖርባቸዋል፣
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- . በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁTir 9 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 0587770371 በመደወል መረጃውን ማግኘት ይችላሉ::
የማቻከል ወረዳ በአማ/ቴ/ሙ/ማሰ/ኮሌጅ