ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 ለብረታ ብረት ስራ ማሰልጠኛ የሚውል ግብዓት
- ሎት 2. ለእንጨት ስራ ማሰልጠኛ የሚውል ግብዓት
- ሎት 3. ለኮንስትራክሽን ማሰልጠኛ የሚውል ግብዓት
- ሎት 4 የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 5. የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትንመስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል ። በዚሁ መሰረት፤
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆኑን ::
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin Number/ማስረጃ የአላቸው ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በጥሬ ገንዘብ /በሲ.ፒ.ኦ/የሚያስይዙ መሆኑን፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 ብር/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ NAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሰትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ መ/ ቤቱ የአዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያውን ሲ.ፒ.ኦ ኦርጂናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታው ውስጥ አስገብተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል ::
- ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመምሪያው ግዥ ፋይ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ሰተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ02/04/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/04/2013 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ መሆኑንና ጨረታው በዚሁ እለት በ16/04/2013 ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች የውል ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ በ5 ቀናት ውስጥ ለአሸነፈበት ዋጋ መጠን 10 % ማስያዝ ይኖርበታል ለማስያዝ ፍቃደኛ ካልሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል ::
- አሸናፊ አቅራቢዎች በዕቃዎች አቀራረብ ላይ የጥራት መጓደል ችግር ቢፈጠር ለውል ማስከበሪያ ካስያዘው ገንዘብ ከመቀጣቱም በተጨማሪ ለተፈጠረው ችግር በህግ ተጠያቂ የሚሆን መሆኑን፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በጥቅል ዋጋ ዝቅተኛ የሰጠ መሆኑ ታውቆ የሁሉም ዕቃዎች ዋጋ መሞላት ይኖርበታል ፡፡
- ለበለጠ መረጃ ካስፈለገዎት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም በስልክ ቁጥር 011 68117 92 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን
የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ