በድጋሚ ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የስኳር ትራንስፖርት አገልግሎት/ማጓጓዝ/ አገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃ/የተወሰነ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ፣ ከወንጂ ዘዴራ/ ስኳር ፋብሪካ፣ ከከሰም ስኳር ፋብሪካ፣ ከናዝሬት ስኳር ፋብሪካ የ45 ቀናት ፍጆታ 2082/ሁለት ሺህ ሰማንያ ሁለት | ኩንታል ሆኖ የአንድ ዓመት 16656 አሥራ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስድስት/ ኩንታል ሆኖ ስኳር ወደ ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ ለሚገኘው የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ለማጓጓዝ ደረጃ 4 የአገር ውስጥ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ካላቸው ባለንብረቶች ጋር ለማጓጓዝ የአገልግሎት በአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የ2012 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና /የምትችል/
- ከሚገዛው የጭነት አገልግሎት ከሚጓጓዘው ጭነት ጋር የተዛመደ ንግድ ሥራ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት Value Aded Tax Certificate ተመዝጋቢ ከሆኑ /የግብር ከፋይነት መስክር ወረቀት (Tax Payer Identification Number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቀሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል /የምትችል/
- ተጫራቾች የማጓጓዝ አገልግሎት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ የጨረታ ሰነድሰቆጣ ከተማ ወይብላ ማርያም አጠገብ ከሚገኘው ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት ሙግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቶች በሌላ ዋጋተመስርቶ መወዳደር የማይቻል መሆኑንና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት እንዲሁም የውል ማስከሪያ ዋስትናው ውል ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10 ቀናት ፀንቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው በታወቁ ባንኮች ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ/ዋናውን የገቢ ደረሰኝ ከማወዳደሪያ ሂሣብ ጋር አብሮ ማስገባት ሲኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡
- ማንኛው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 5/አምስት ቀናት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሰቆጣ ከተማ ወይብላ ማርያም በስተጀርባ ከሚገኘው ዋቢ/ሁለገብ/የገ/ህ/ስ/ማ ኃላፊነቱ የተወሰነ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ6 ቀን /ስድስተኛው ቀን/ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋቢ ሁለገብ /የገ/ህ/ስ/ማ ኃላፊነቱ የተወሰነ ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በተከታታይ 6/ስድስተኛው ቀን /ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽገው ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ለማሻሻል ወይንም ከጨረታው ለመውጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ ማወዳደያ ሀሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው 2 ቀን /ሁለት ቀን በፊት/ በጽሑፍ ሊያሳውቁ ይገባል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቶች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች ስለ ጨረታው ዘርዝር መረጃ ከፈለጉ ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማህበር ኃላፊነት የወሰነ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 03344011773 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር