በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት አማካኝነት በ2013 ዓ/ም በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- በደረጃ አንድ ኤሌክትሮኒክስ፣
- በደረጃ ሁለት የሠራተኞች የደንብ ልብስ የተዘጋጁ እና ብትን ጨርቅ እንዲሁም ጫማ፣
- በደረጃ ሶስት የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፤
- በደረጃ አራት የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚቻል ሲሆን የደንብ ልብስ፣ ብትንና የተዘጋጀ ጨርቅ፣ ጫማ ተጫራቹ ናሙና ከጽ/ቤቱ በቀረበው ናሙና መሰረት በማየት ማቅረብ ያለበት ሲሆን ጠቅላላ በእያንዳንዱ የተገለፁት አሸናፊው የሚለየው ከመኪና መለዋወጫ እቃ ውጭ ያሉትን በሎት ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡
- ተጫቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር የእያንዳንዱ በደረጃ ተለይቶ የተዘረዘረውን ዕቃ 50 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚፈልጉ በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከ23/02/2013 ዓ/ም እስከ 7/03/2013 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ 07/03/2013 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የኤሌክትሮኒክስ፣ የደንብ ልብስ፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ የስፖርት ትጥቅ 8/03/2013 ዓ/ም 3፡30 ተዘግቶ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በ16ኛው በ4፡00 ጀምሮ ከላይ በማስታወቂያው ላይ በደረጃ በቅደም ተከተል በተቀመጠው መሠረት ይከፈታል፤
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በለሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፈት ስልጣን አለዉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራቾች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ዉሰጥ የአሸነፈዉን ዕቃ ምስ/ደ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚኖርበት ሲሆን የመኪና መለዋወጫ እቃ ግዥ አሸናፊው የሚለየው በለቀማ መሆኑ መታወቅ ያለበት ሲሆን ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2013 ዓ/ም ውል ተወስዶ መኪና ሲበላሽ የሚፈለገውን የመኪና እቃ በሙሉ መሰረት ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918739006/0583350601 በመደወል ማግኘት ይችላሉ
- ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ ወይም የዕቃ አቅርቦት ችግር የአለባቸውን ተጫራቾች አይጋብዝም፡፡
የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር
ጽ/ቤት