Cleaning and Janitorial Equipment and Service / Garments and Uniforms

በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ጤና መምሪያ መካነ-ሠላም ሆስፒታል የላውንደሪ ሥራን ኣውት ሰርስ በማድረግ በግለጽ ጨረታ አወዳድሮ ለኣንድ ዓመት ቆይታ ማስራት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ጤና መምሪያ መካነ-ሠላም ሆስፒታል የላውንደሪ ሥራን ኣውት ሰርስ በማድረግ በግለጽ ጨረታ አወዳድሮ ለኣንድ ዓመት ቆይታ ማስራት ይፈልጋል። 

 1. የመካነ-ሠላም ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በአጠቃላይ የአገልግሎት መስጫ ከፍሎችንና ከልሉን በሙሉ ንብረትና ደህንነቱን የሚጠብቅ። 
 2. በጥቃቅንና አነስተኛ ህግ በሚያዘው መሰረት የተደራጀና መረጃ ማቅረብ የሚችል ይበረታታል። 
 3. ቫት ተመዝጋቢ /ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆነ/ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው። 
 4. በሁለቱም መግቢያና መውጫ በሮች በመመሪያው መሰረት ፍተሻ በማድረግ በአግባቡ ማስተናገድ አለበት። 
 5. በጥበቃ ስራ ላይ የሠራተኛ ብዛት 12፣ በላውንደሪ ስራ ላይ የሠራተኛ ብዛት 6 እና የፅዳት ሠራተኞች ብዛት 12 የሚሆኑና ቅዳሜ፣ እሁድ የህዝብ በአላትና የአዘቦት ቀን በ24 ሰዓት ውስጥ በጥበቃና በላውንደሪ እንዲሁም በፅዳት ስራ ላይ በተሟላ ሁኔታ ላይ በመገኘት ማጠብ፣ መጠበቅና ማፅዳት አለባቸው። 
 6. አሸናፊው ተጫራች (ማህበሩ) በጥበቃ ወቅት በሁሉም በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢና የላውንደሪ፣ የፅዳት ስራ መስጫ መስጫ ክፍሎች የሚገኙ ንብረቶችን በአግባቡ ባለመጠበቅና በእንዝላልነት በግዴለሽነት ምክንያት ለሚጠፉ ንበረቶች የመንግስትን ሀብትና ንብረት የሚከፈልና በህግ የሚጠየቅ መሆኑን። 
 7. በሆስፒታሉ ህግና ደንብ መሰረት ተገዥ የሆነና ሌሎች ከጥበቃና ስራ ከፅዳት ሥራ፣ ከላውንደሪ ስራ ጋር የተያያዙ ስራዎችንና የሚሰጠውን ማንኛውንም ተግባር ተቀብሎ መፈፀም የሚችል። 
 8. አሸናፊው ድርጀት /ማህበሩ በሚያሰራው የጥበቃና በላውንደሪ እንዲሁም በፅዳት ሠራተኛ የሚፈጠር ማንኛውንም ችግር ተጠያቄ ይሆናል:: በወር የአገልግሎት ክፍያና ደመወዝና በዓመት ሁለት ጊዜ ለደንብ ልብስ ግዥ ጨምሮ የላውንደሪ ማጠቢያ እቃወችን የፅዳት እቃዎች ግዥ መጠየቂያ ደመወዝ ጭምር ሊከፈለው የሚችለውን የገንዘብ መጠን ጥቅል ድምር በተዘጋጀው የመወዳደሪ ሰነድ መሙላት አለበት። 
 9. የተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 ሃምሳ ብር በመክፈል ከመካነ-ሠላም ሆስፒታል ዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት ይቻላል። በጥቃቅን የተደራጁ በነፃ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት 2% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያ አለባቸው። 
 10. ማንኛውም ተጫራች በተዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በደንብ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ዘወትር በስራ ሰዓት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት በግዥ ኦፊሰር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል። ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችን በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። 16ተኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በአላት ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታውን መክፈት ይቻላል። ማንኛውም የላውንደሪ እጥበት ስራ እቃዎች በረኪና፣ ኦሞ፣ ላርጎ፣ ሳሙና፣ የእጅ ጓንት ለስራው የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች በራሱ ወጭ አሟልቶ ማጠብ የሚችል። የላውንደሪ ስራ ላይ የስራ ክፍሎች የሚገኙትን እንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ ኦአርሳይ ያሉ የተለያዩ ልብሶች የባለሙያ ጋወን ሌሎችም መታጠብ የሚያስፈልጋቸው ልብሶችን የበረኪና አንድ ለዘጠኝ ውህድ በመጠቀም በእጅ ማጠብ የሚችል ማንኛውንም ያፅዳት እቃቸው- ለምሳሌ በረኪና ፣ አሞ፣ ላርጎ፣ ቪም፣ ድቶል፣ የፕላስቲክ መጠረጊያ፣ መወልወያ እና ባልድ፣ ፎጣ በራሱ ወጭ አሟልቶ ማፅዳት የሽንት ቤት መርዝ በመጠቀም የመፀዳጃያ ቤት ሽታ አልባ ማድረግ የሚችል መሆን አለበት፡፡ 
 11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 • ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ መረጃ ከፈለጉ መ/ሠሆስፒታል ከግ/ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 
 • ቁጥር 09 85 14 98 75/09 14 34 43 06 ወይም 033 220 08 34በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል። 

የመካነ-ሠላም ሆስፒታል