ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ (ወሎ መስ/ዞን ፖሊስ መምሪያ የግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት በፑል አገልግሎት ለሚሠጣቸው ለ2ኛ ብርጌድ አድማ ብተና ፖሊስ፣ ለደሴ ከተማ አስ/ፖሊስ መምሪያ እና ለአባይ ብርጌድ ልዩ ሀይል ፖሊስ አገልግሎት የሚውሉ፡
- 1ኛ. የፅህፈት መሣሪያ እና ቋሚ እቃዎች
- 2ኛ. የተሽከርካሪ መለዋዎጫዎች
- 3ኛ. የመኪና ጎማዎች
- 4ኛ. የማብሰያ መመገቢያ እቃዎች
- 5ኛ. የህንፃ መሣሪያዎችን
- 6ኛ. የፅዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የሚከተሉትን ግዴታዎች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
- 1ኛ. ተጫራቾች አግባብ ያለው /በዘርፉ የተሠማሩበትን የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- 2ኛ. የቲን ምዝገባ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- 3ኛ. የግዥው መጠን ከ50,000 ሺ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- 4ኛ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከ-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዎቻቸውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ኢያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታው መክፈቻ ዕለት ኦርጅናሉን ሲጠየቁ ማሳየት አለባቸው፡፡
- 5ኛ የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- 6ኛ. ተጫራቾች ከተ/ቁ 1-5 ያሉትን ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ተ/ቁ 6 የተመለከተውን በብር 25.00/ሃያ አምስት ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
- 7ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- 8ኛ. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ሁለት ፖስታ ደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- 9ኛ. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- 10ኛ. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- 11ኛ. መ/ቤቱ፡ ጨረታውን 20% ጨምሮም ሆነ ቀንሶ ሊገዛ ይችላል፡፡
- 12ኛ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-37 03 በመደወል ማግኘት ይችላሉ: አድራሻ፡ ደሴ ቧንቧ ውሃ ሜልቦርን ሆቴል ፊትለፊት ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስ ደጋፊ/የስራ ሂደት