Foodstuff and Drinks

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሸጋው ሞጣ የመጀ/ደ/ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ በሽተኞችምግብ የሚያቀርብ ለአንድ ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስቀረብ ይፈልጋል

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሸጋው ሞጣ የመጀ/ደ/ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ በሽተኞችምግብ የሚያቀርብ ለአንድ ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስቀረብ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም

 1.  ተጫራቾች አገልግሎቾችን ለማቅረብ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያወጡና የተሰጣቸውን ፈቃድ አንድአመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ካርድ/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት እናየግዥው መጠን ብር 200,000.00 እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነትየተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዦዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸውቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸውእርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በግልፅ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውምተጫራች በጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ 40.00 በመክፈል ከግዥ/ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ሰነዱንከዋና ገዘብ ያዥ በመጠየቅ መግዛት ይቻላል፡፡
 4. . በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
 5. . ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
 6. . ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 40.00 ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
 7. . ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማረኛ መሆንይኖርበታል፡፡
 8. . በዚህ ጨረታ መጫረት የምትፈልጉ በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል በመጨረሻው በ 16ኛው ቀን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባትይቻላል፡፡
 9. . ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዶቻቸው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጨረታ ማስታወቂያበተገለፀው ቦታ ቀንና ስዓት መሰረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የመጫረቻ ሰነዶች ብዛትያላቸው ከሆነ በጨረታ ሳጥኑ ማስገባት አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ ለግዥ ኦፊሰር በእጃቸውማስረከብ ይችላሉ፡፡ ተረካቢውም የተጫራቹን ስምና አድራሻ እንዲሁም የተረከበበትን ቀንና ስዓትየሚገልፅ ማስረጃ ወይም ደረሰኝ ይሰጣል፡፡
 10. . ጨረታው በተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸ/ሞ/የመ/ደ/ሆስፒታል በ16ኛውቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ይከፈታል፡፡
 11.  አንድ ተጫራች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግ ጨረታውንላወጣው መስሪያ ቤት በፅሁፍ ወይም በፋክስ ቁጥር 0586610264 ወይም በስልክ ቁጥር0586610330 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤትም የተጠየቀውንጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሁፍ ወይም በፋክስ ጨረታውከመከፈቱ ከ5 ቀናት በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
 12. . መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 13. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡
 14. ለሚቀጥራቸው ሰራተኛ የደንብ ልብስ ማሰፋት የሚችል እና በየ3ወሩ የጤና ምርመራ በራሱ ወጭማስመርመር የሚችል
 15. . የማብሰያ ምግብ አዳራሹን ሆስፒታሉ ይሸፍናል፣ የመገልገያ እቃዎችን እራሱ ችሎ መስራትየሚችል እና ምግብ ሲበሰል በመብራት በመሆኑ መብራት በሚጠቀሙበት ወቅት የተጠቀሙበትንመብራት ቆጣሪ የሚከፍል
 16. . የምግብ ጥራት ኮሚቴው አስተያየት ሲሰጥ ፈጥኖ የማስተካከያ እርምጃ የሚወስድ መሆን አለበት
 17. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድ ቅዳሜና በዝግ ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተጠየቀው ስዓትሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን
 18. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000.00 ማስያዝ አለባቸው፡፡

የሸጋው ሞጣ የመጀ/ደ/ሆስፒታል