ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የማዕ/ጐን/መስ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት የምዕ/በ/ወ/ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 2 የደንብ ልብሶችን
- ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 4 የተለያዩ ህትመቶችን፣ እንዲሁም
- ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጨማሪ የግዥ ብር መጠን 200 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ በተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 10 በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ መ/ቤቱ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓትመውሰድ ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ የእቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር መጠን ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ምዕ/በለሣ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ከ23/02/2013 ዓ/ም እስከ 07/03/2013 ዓ/ም ለተከታታይ 15 ቀን እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለዕቃው አይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል መሣተፍ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችሉም፡፡
- መስሪያ ቤቱ ዕቃዎችን 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕ/በለሣ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር በ08/03/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ታሽጐ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል/ዝግ/ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ምዕ/በለሣ ወረዳ ፍ/ቤት ማቅረብ የሚችል መሆ ን አለበት፡፡
- ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ምዕ/በ/ወ/ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918382904በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ፖስታ ላይ ስሙን እና አድራሻውን እንዲሁም ስልክ ቁጥሩን እና የድርጅቱን ማህተም በፖስታው ላይ ማስቀመጥ እንዳለበት እና በሁሉም ሰነዶች ገጽ ላይ ፊርማና ማህተምማስቀመጥ አለበት፡፡
የምዕራብ በለሣ ወረዳ ፍ/ቤት