የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/ቁ/01/13
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የላልይበላ/ከ/አስ/ርከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ት/ጽ/ቤት ስር የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በCIP በተያዘ በጀት በሮሀ ቀበሌ Basement+G+2 ቢሮ ግንባታ የዲዛይንና የማማከር ስራ ለሚሰሩ ተቋራጭ ደረጃ 6 እና በላይ እንዲሁም ለጽ/ቤታችን አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ (ሎት)እና የጽህፈት መሳሪያ (ሎት2) ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ካሸናፊው ውል በመያዝ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- ተጫራቶች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነበር፣ የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የብቃት ማረጋገጫና የ2012 ዓ.ም ግብር የከፈሉበትን የግብር ከሊራንስ ወረቀት ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሚጫረቱባቸው ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የንግድ ስራ ፍቃዳቸውን ላይ በጀርባው ያለውን አብረው ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ለዲዛይንና ማማከር ተጫራቶች ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ከመጀመሪያው ቀን ከ3/1/2013 ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ22ኛው ቀን ማለትም በ25/01/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቶች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በላልይበላ ከተማ አስተዳደር ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ት/ጽ/ቤት /የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ኤሌክትሮኒክስ እና የጽህፈት መሳሪያ ለሚጫረቱ ተጫራቾች ደግሞ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ከመጀመሪያውን ቀን በ3/1/2013 ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ማለትም 18/01/13 ዓ.ም ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
- ለዲዛይንና ማማከር ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ከ3/1/2013 ዓ ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን ከ11፡30 ሰዓት ድረስ በላልይበላ ከተማ አስተዳደር ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ት/ጽ/ቤት/የግ/ፋይ/ንብ/ አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን ኤሌክትሮኒክስ እና የጽህፈት መሳሪያ ለሚጫረቱ ተጫራቾች ደግሞ በተራ ቁጥር 4 ላይ ከተገለጸው ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን 11፡ 30 ሰዓት ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በብር 100 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- የዲዛይንና ማማከር የጨረታ ሰነዱ የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5166 (አምስት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ስድስት) ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ለኤሌክትሮኒክስ እና የጽህፈት መሳሪያ ለሚጫረቱ ተጫራቾች ደግሞ ለሎት(1) ብር 5982 (አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሁለት ) 1940 (አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ አርባ ብር) ማስያዝ አለባቸው።
- (ዛይንና ምክር ተጫራች የእረታ ሃሳቡን 1 ወይም ወጥ በሆነ 2ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት ለቴክኒካልና ለፋይናንሽያል ለእያንዳንዳቸው ለየብቻ በጥንቃቱ በታሸገ ፖስታ የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ከ አገ/ት/ጽ/ቤት የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን የጨረታ ኮሚቴው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 25/1/2013 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ለኤሌክትሮኒክስ እና ጽህፈት መሳሪያ ተጫራቾች ደግሞ ዋና እና ቅጅ በማለት እስከ 18/01/ 13 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ከሆኑ ተጫራች ለሚሰራው የዲዛይንና ማማከር ስራ እንዲሁም ለሚያቀርበው ዕቃ 100% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በፍትህ ጽ/ቤት በመቅረብ ቅድሚያ ውለታ መውሰድ አለበት።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን የዲዛይንና ማማከር ስራ እንዲሁም ለሚቀርበው ዕቃ በውሉና በስራ ዝርዝሩ እንዲሁም በስፔስፊኬሽን መሰረት በጥራት ካላስረከበ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ውርስ ይሆናል
- ተጫራቶች ያሸንፉትን የኤሌክትሮኒክስ እና የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች በራሳቸው በአሸናፊዎቹ ሙሉ ወጪ የላልይበላ ከተ/አስ/ር/ከ/ል/ቤ/ ኮ አገ/ት/ጽ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቶች በጨረታው ላይ ማብራሪያ/ማሻሻያ/ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው የጊዜ ገደብ ከ3 ቀን በፊት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ከተገለጸው ቀን በኋላ ጥያቄ ቢያቀርቡ ተቀባይነት የለውም።
- የኤሌክትሮኒክስ እና የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች የጨረታ ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ40 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን የዲዛይንና ማማከር ስራ ደግሞ ለ60 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- ተጫራቶች ከዚህ በፊት በጨረታ አሸናፊ ሆነው እንደውላቸው ያላጠናቀቁ ወይም ከታወቀ ተቋም ዕገዳ የተደረገባቸውን አያሳትፍም።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ ማድረግና የጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ሳይሞሉ ክፍት ማድረግ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ኣማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም
- በስልክ ቁጥር 03333360016/0333360728 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የላልይበላ ከተማ አስተዳደር ቤቶች
ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት