የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
1.በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአምራችና ጅምላ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት1 :- ልዩ ልዩ የግብርና ኬሚካሎችና/ጸረ–ነፍሳት፣ጸረ–አረምና ጸረ–ፈንገስ
- ሎት2፡– ልዩ ልዩ የጓሮ አትክልት ዘሮች
- ለት፡-3 ልዩ ልዩ መገልገያ መሳሪያዎች (ማጭድ፣መርጫ መሳሪያ፣ትጥቅ ልብስና የነቀዝ ፒክስ)
- ሎት 4 ለእንሰሳት መኖ የሚውል ጥሬ እቃ የዶሮ ኮንሰንትሬት/
- ሎት:-5 ልዩ ልዩ ሰብሎች/ስንዴ፣ ዱቤ ሽምብራ ፣ የአካባቢ ሽምብራ ፣ ባቄላ ፣ አተርና ተልሳ ሽያጭ
- ሎት፡– 6 የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ (ፉርሽካ) ሽያጭ ስለዚህ የሚከተለትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በእነዚህ ንግድ ዘርፍ ዘርፎች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ያለው፡፡
- የበጀት ዓመቱን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ቲን–ነምበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን የታደሱ ማስረጃዎች ፎቶ–ኮፒ ማቅረብ አለባቸው::
- ለእያንዳንዱ ሎት ዝርዝር መግለጫ እስፔሲፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል በወደራ ሁለገብ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃላተ ስም በአካውንት ቁጥር 1000082689967 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠባሴ ቅርንጫፍ በማስገባት እና ያስገቡትን የባንክ ደረሰኝ በመያዝ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ ኣካባቢ ከመልዕክት ኣካዳሚ ጎን እና ህዳሴ የመኪና ማሰልጠኛ ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበረት ዩኒዬን ኃላ.የተ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ዋጋው 2% /ሲፒኦ/ ዋስትና በባንክ በተረገገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/በሁለት ፈራሚ የተረጋገጠ በደ/ ብርሃን ከተማ ባሉ ባንኮች በዩኒዬኑ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዶክመንት ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በሁለት ፖስታዎች ተለያይቶ እና አሸጎ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን እና ህዳሴ የመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃሏየተ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት (ቅዳሜን እስከ 6:30 ጨምሮ) ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 10ኛ ቀን የስራ ቀናት (ቅዳሜን ጨምሮ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ8:00 ድረስ ማስገባት ይቻላል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን እና ህዳሴ የመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላያተ ጽ/ቤት በ10ኛው ቀን/የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 8፡30 ሰዓት ይከፈታል::
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን እና ህዳሴ የመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላያተ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 011 681 41 15 /011 681 63 85 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር
ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህ/ስ/ማህበራት ዩኒያን ኃላ/የተ
ደ/ብርሃን