Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others / Vehicle

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የራቤል ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2013 በጀት አመት ለራቤል ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት ፈልጎ የማሽነሪ ኪራይ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዶዘር፤ ግሬደር ፤ ዳምፕ ትራክ ፤ እስካቫተር በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

የግልጽ ጨረታ ማስታዎቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የራቤል ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2013 በጀት አመት ለራቤል ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት ፈልጎ የማሽነሪ ኪራይ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዶዘር፤ ግሬደር፤ዳምፕ ትራክ ፤ እስካቫተር በግልጽ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

 1. በዘመኑ የታክስ  አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው/ያላት
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላት ያለው
 3. የግዥው መጠን ከብር 50000/ሃምሳ ሺ ብር / በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ከፋይነት ተመዝጋቢ የሆነ እና ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልጽ የሚነበቡ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 30 ግሼ ወረዳ መሪ ማዘጋጃ ቤት ፋ/ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
 6. የሚገዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 1ፐርሰንት በሲፒኦ /በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል
 8. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ የህዝብ በአላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይሆናል
 9. ሎት2 ዶዘር ፤ሎደር ፤ሮሎ እና ሲኖ ትራክ/ዳም ትራክ ማሽን ኪራይ ጨረታው የሚዘጋው በ22 ቀን 3፡00 በ22 ቀን 4፡00 ይከፈታል ፡፡
 10.  ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 11. ካት ዶዘር D8R 200ሰዓት መስራት የሚችል፤ሎደር 100 ሰዓት መስራት የሚችል፤ሲኖትራክ ዳም ትራክ 400 ዳምፕ መስራት የሚችል እንዲሁም 3 እና ከዚያ በላይ ሲኖትራክ ማቅረብ የሚችል ፤ሮሎ 100 ሰዓት መስራት የሚችል ዝርዝር የማሽን ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል
 12. ጽ/ቤቱ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው
 13. ማንኛውም ተጫራች ግዥ/አገልግሎቱ በጥቅል በሎት ስለሆነ ከተዘጋጀው ዝርዝር ዕቃ ውስጥ ካልሞላ ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
 14. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡ የዶዘር ግሬደር፤ ሲኖትራክዳምትራክ፤ ሎደርና ሮሎ የማምጫና የመመለሻ ወጪን አሸናፊ ድርጀቱ ይሸፍናል፡፡
 15. . በጨረታው ቀን ተጫራቹ /ህጋዊ ወኪሉ ባይገኝም ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡
 16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 17. ሊብሬ ማቅረብ የሚቻለው ካሸነፈ በኋላ ውለታ ላይ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 18. . ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0900109316/0922903286

በአብክመ የሰሜን ሸዋ ዞን የራቤል ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት