ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር =ብ/ግ/ጨ/መደ/03/3
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን መስተዳድር ውስጥ የሚገኘው የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለወረዳዉ ተሸከርካሪዎች የሚሆን መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለአንድ ዓመት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆኑ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- . የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ዋጋው ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የሚወዳደሩት ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- . ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነጻ ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ዘውትር በስራ ስዓት ከ23/02/2013 ዓ.ም እስከ 07/03/2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ ሰነዱን በነጻ በመዉሰድ ዋጋቸዉንበመሙላት ቢሮ ቁጥር 7 ከተዘጋጀዉ ሳጥን በመክተት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ በለሉበት ሰነዱ ተሟልቶ ከተገኘ በ08/03/2013 ዓ.ም የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 3፡35 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቹ በራሱምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኝ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ኮፒውን ከኦርጅናሉ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ቅድመ ክፍያ መውሰድ የሚፈልግ ከሆነ በሚወስደው የቅድመ ክፍያ የገንዘብ መጠን ተመጣጣኝ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታ አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
- . መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583320175 ወይም 0918725154 /0913071630 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የጎንደር ዙሪያ ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት