የካፍቴሪያና የሱቅ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ካፌ/ኪሪ/ጨ/አስ/አሃሪ/ሠሪ/መ/ ዕድር/001/2012
በአለርት ማዕከል ግቢ ውስጥ የሚገኘው አለርት ሠራተኞች መረዳጃ ዕድር ካፍቴሪያ ለካፍቴሪያና ምግብ ቤት አገልግሎት የሚውል ከነ ሙሉ መገልገያ ዕቃዎች እንዲሁም ለሱቅ አገልግሎት የሚውል ቤት በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ቀርበው በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1.ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የሰነድ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ኮፒ በማድረግ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በዘርፉ የተሠማሩበት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ
- የግብር ከፋይ (TIN) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤
2. ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን ለጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለአለርት ሠራተኞች መረዳጃ ዕድር በሚል ስም የተዘጋጀ ሲፒኦ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚገልጸውን ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 300.00 (ብር ሦስት መቶ) በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ግዥ አስተዳደር ቡድን ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል ሆኖም የጨረታ መክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በማግስቱ በስራ ቀን ይከፈታል ፤ ተጨማሪ ቀን ካስፈለገ ሁሉም ተሳታፊ ተጫራቶች በደብዳቤ እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡
5 በካፍቴሪያው እና በሱቁ ውስጥ ለአገልግሎት የማይቀርቡ በህግ የተከለከሉ መያዝ የሌለባቸው ነገሮች እንደ ጫት፣ ሲጋራ፣የአልኮል መጠጥ ማቅረብ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት የዋጋ ዝርዝር የተሞላበት ፋይናንሺያል ሠነዳቸውን ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች ለማዕከሉ ሠራተኞች የሚያስተናግዱበትን የዋጋ ዝርዝር ከሰነዳቸው ጋር አብረው ሊያቀርቡ ይገባል፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው ቀን እና ሰዓት በአለርት ሠራተኞች መረዳጃ እድር ካፍቴሪያ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ላይ በእለቱ ይከፈታል የመከፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡
9 ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
ማሳሰቢያ፡– የአለርት ሠራተኞች መረዳጃ እድር የተሻለ መንገድ ካገኘ
ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፤ በስልክ ቁጥር፡– 0118356784 ደውለው ይጠይቁ፡፡
የአለርት ሠራተኞች መረዳጃ ዕድር