የግዥ መለያ ቁጥር 01/2013
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ ወ.01 ጀሞ አካባቢ የቡርቃ ዋዮ ቁ.2 /የመ/ደ/ት/ቤት የ2013 ዓ.ም በጀት ኣመት የሚገዙ ዕቃዎች
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 ቋሚ እቃዎች
- ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 4 የደንብ ልብስ
- ሎት 5 የህትመት ስራ
- ሎት 6 የጥገና እቃዎች ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት:
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ 5000 ብር በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከተደራጁበት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ከሆነ
- ተጫራቾች ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) ብር-በመከፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወ 01 ኣካባቢ ስፕሪንግ ኦፍ ኖውሌጅ አካዳሚ ት/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው የቡ/ዋ/ቁ2/ የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ፋይናንስ ና ግዥ ቢሮ ቁጥር 2 ለጫረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10 ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ ልክ በ4፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ከሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት1፣ ሎት 3፣ ሎት 4 ፣ ሎት 5 እና ሎት 6 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለ ሎት 2 በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት ያሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- . መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ክ/ከ ወ 01 ጀሞ አካባቢ ከሸራ መስኪድ ዝቅ ብሎ ስፕሪንግ ኦፍ ኖውሌጅ ት/ቤት ፊት ለፊት የቡ/ዋ/ቀ.2 የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 2
| ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118445807/018445516
በን/ስ/ላ/ክ/ከ ወ01 ጀሞ አካባቢ የቡርቃ ዋድ ቀ.2 /የመ/ደ/ት/ቤት