ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በስሩ ለሚገኙ ለ7ቱ ፖሊስ ጣቢያዎች በ2012 ዓ.ም በጀት አመት የሚያስፈልጋቸውን
- ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ
- ሎት 2. የፅዳት ዕቃ
- ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 4 የህንፃ መሣሪያ
- ሎት5. አልባሳት
- ሎት6. የህክምና መድኃኒት
- ሎት7. የመኪና ጎማ
- ሎት 8. የእስረኛ ቀለብ
- ሎት 9. ህትመት
- ሎት 10. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆነው በስራ መስኩ የተሰማሩ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግስትግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ለሎት ፡2፣4፣10 ለእያንዳንዱ ሎት 2,000.00/ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 1፤5፣ 6፣7፣8 ለእያንዳንዱ ሎት 3,000.00/ሦስት ሺህ ብር/ ለሎት 3 እና 9 ለእያንዳንዱ ሎት 5,000.00/ አምስት ሺህ ብር/ ሲፒኦ /CPO/ በመ/ቤታችን ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለአንድ ሎት የማይመለስ 100.00 / መቶ ብር/ በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ ፖሊስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከአንድ ሎት በላይ ሲወዳደሩ በእያንዳንዱ ሎት ከላይ በተቁ 1 ላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች አሟልቶና አያይዞ በየሎቱ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በክ/ከተማው የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን መ/ቤቱ መመዘኛ መስፈርት /Specification/ ባወጣንባቸው ዕቃዎች ላይ ሌላ የራስን መመዘኛ /Spec/ አውጥቶ መወዳደር አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ 10% ዋስትና መስጠት ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ
በስልክ ቁጥር :011-442-33-15/011-443-1529/011-833-41-10 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአ/አ/ከተማ አስ/ፖሊስ ኮሚሽን