በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ
የ2013 ዓ.ም በድጋሚ የወጣ የመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ
ለ2013 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውል
- መድሃኒት፣
- የህትመት ውጤት ፤
- ቋሚ የህክምና ዕቃዎችና
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡
- ተጫራቾች በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5,000.00/ አምስት ሺህ/ ብር CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን 100.00/አንድ መቶ/ ብር በመያዝ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾቹ በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመነ የግብር ለመክፈላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ፋይናንስ ቢሮ ቁTir 410 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ናሙና አይነት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- በተጫራች የሚሞላው የዋጋ ዝርዝር ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን እለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በጤና ጣቢያው አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አሟልተው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ ፡–በን/ስ/ላ/ክ/ከ ወረዳ 10 ጤ/ጣቢያ ቦታ
ብሔረ ፅጌ ማርያም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወረድ ብሎ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁTir 0118898640 ይደውሉ።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ
[embedded content]