ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 006/2013
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስር ላሉት ጽሕፈት ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን
- ሎት 1 ፤ መስተንግዶ፣
- ሎት2፤ ህትመት በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሳተፍ ይፈልጋል በዚህም
መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ/ ሎት 1፤መስተንግዶ ብር 5000.00 (አምስት ሺ) ሎት 2፤ ህትመት ብር 5000.00 (አምስት ሺ ብር) ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በየሎቱ በመከፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 5 የሥራ ቀናት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአምስተኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ6ኛው ቀን 4፡30 በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳ ወጣት ማዕከል መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎቶች ሁሉ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ በጨረታ ተቀባይነት የለውም፡
- አሸናፊ ተጫራቶች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቶች በተጨማሪም ለህትመት ዕቃዎች ሳምፕል ለሚያቀርቡት ዕቃዎች በሙሉ እያንዳንዱ ዕቃ ላይ የራሳቸውን ማህተም መለጠፍ አለባቸው፡፡
- በተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት
- የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡- 0944087775 ወይም 0910574633
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ
08 አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ