ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 01/1534/12
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ጽህፈት ቤት ስር ላሉት ጽህፈት ቤቶች በ2013 በጀት አመት የሚያስፈልጋቸውን
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 ቋሚ እቃዎች
- ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 4 የደንብ ልብስ
- ሎት 5 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ሎት 6. የህትመት ስራ
- ሎት 7 የኤሌከትሮኒከና የቢሮ እቃዎች ጥገና
- ሎት 8 የመስተንግዶ አገልግሎት
- ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል በዚህም መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በየሎቱ በመከፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ11፡00 ሰአት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታሳጥንከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት01፣ ሎት 3፣ ሎት 4፣ ሎት 5፣እና ሎት 6 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 7፣ ለሎት 8 በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም ለሎት 6 ከጀርባው በተያያዘው እስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ኣሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
በተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ–
አድራሻ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ካዲስኮ አዋሽ ባንክ ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ
የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡– 011-8-88 65-32/0118885787
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07
አስተዳደር ጽህፈት ቤት