ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2013 ዓ.ም
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ጽ/ቤት የኮሮና ቫይረስ/COVD 19/ መከላከያ ግብዓቶችን የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች እና የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር እቃዎችን ለማስጠገን እንዲሁም ፍርስራሽ ቆርቆሮዎችን ለመሸጥ ከሚከተሉት ከህጋዊ ተወዳዳሪዎች አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን እንዲሁም ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሎት |
የአገልግሎት ዝርዝር |
የሲፒኦ መጠን |
ሎት 1 |
የኮሮና ቫይረስ/CoVD 19 መከላከያ ግብዓቶች ግዢ |
1000 |
ሎት 2 |
የሚጠገኑ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
1000 |
ሎት 3 |
የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር እቃዎችን ጥገና |
1000 |
ሎት 4 |
ፍርስራሽ ቆርቆሮዎች ሽያጭ |
2000 |
ስለሆነም ከተራ ቁጥር 1-4 ለተጠቀሱት እቃዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ ቲን–ነምበር ያለው በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከተደራጀበት መስሪያ ቤት የተለያዩ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሰውን እቃ የአንዱን መለኪያ ዋጋ ቫቱ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ በዋለ 11 የስራ ቀናት ሲሆን ልክ 4፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ካደራጀው መስሪያ ቤት የጨረታ ማስከበሪያና የውል ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ በዋለ በ11ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ 5000 (አምስት ሺህ ብር ) በሲፒኦ ብቻ በመስሪያ ቤቱ ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ መጥተው በ100 (መቶ ብር በመግዛት መውሰድ የሚችሉ መሆኑንና ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በማሸግ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸበት እለት ጀምሮ ባሉት ሰባት ቀናቶች ውስጥ ውል በመፈጸም የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ሲፒኦ ሲያሰሩ ከላይ ሰንጠረዥ ውስጥ በተቀመጠው መሰረት በሚገዙት ሎት መጠን ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡– ማንኛውም በጨረታው የሚሳተፍ ህጋዊ ተወዳዳሪ በሰነዱ ላይ ከተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ውጪ መጠቀም ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
አድራሻ፡– ከመገናኛ ጎሮ አደባባይ ወደ ሰሚት በሚወስደው መንገድ ፍሊንት ስቶን ሳይት ሳይደርሱ ከድልድዩ አጠገብ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0118932851
የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት