በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳደር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ የህትመት ስራዎች : የህክምና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Tender
< Back

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳደር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ የህትመት ስራዎች : የህክምና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 003/2012 

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳደር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

 1. ሎት 1 የህትመት ስራዎች የጨረታ ማስከበሪያ 4000.00 (አራት ሺህ ብር) 
 2. ሎት 2 የህክምና ዕቃዎች 8000.00 (ስምንት ሺህ ብር) 

በመንግስት ግዥና ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ። 

 1.  ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድና በንግድ አዋጅ መሰረት ምዝገባ ያካሄደ እና የዕቃ አቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ከወጣው ጨረታ ውስጥ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 
 2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር እንደየሎቱ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው::
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በየሎቱ የማይመለስ ብር 100.00 (ብር መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
 4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ በ2 ኮፒ ማድረግ ከ2፡30-1፡00 ሰዓት ለዚህ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
 5. የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
 6. ፎቶ ኮፒውን በአንድ ፖስታ፣ ዋናውን በአንድ ፖስታ ተደርጎ ፖስታው ላይ ዋና ወይም ፎቶ ኮፒ ተብሎ ይገለጽ። 
 7. ጨረታው በ6ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐበዚያው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። – 
 8. ከወጣው ጨረታ ብዛት ላይ መ/ቤት 20 በመቶ የመጨመር 20 በመቶ የመቀነስ መብት አለው:: .
 9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው:: አሸናፊ ተጫራች ባመጣው ናሙና መሰረት ዕቃውን ማቅረብ ይጠበቅበታል። ቋሚ ዕቃዎችን መ/ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል። 
 10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ስከልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በቀረበው ሎት መሠረት ፖስታ ላይ መገለጽ ይኖርበታል። 
 12. ተጫራቾች ለአሸነፉበት ዕቃ ዋጋ 10% CPO ማስያዝ አለባቸው።
 13. በራሳቸው ትራንስፖርት የጨረታ አሸናፊ ድርጅት መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል። 
 14. በማስታወቂያው ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሠረት ተፈጻሚ ይሆናሉ። 

አድራሻ፡- ከኢምፔሪያል 100 ሜትር ገባ ብሎ ሳሚ ሕንፃ ፊት ለፊት ኬቢ የአሽከርካሪ ማሠልጠኛ ጀርባ መሆኑን እንገልጻለን። ተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 011 8 22 99 52 ይደውሉ። 

በአዲስ አበባ ከተማ የቦሌ ክፍስ ከተማ አስተዳደር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ