ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስ/ጐጃም ዞን በብቸና ማረሚያ ቤት የ2013 በጀት አመት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ዕቃዎች ምድብ
- ለምግብ አገልገሎት የሚውል ቀይ ጤፍ ፣ ነጭ በቆሎ ለእንጀራ፣ ባቄላ፣አተር ፣ ምስር፣ ክክ ቅመማ ቅመም፣ በርበሬ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ፣ የማገዶ እንጨት እና ሌሎችንም ምድብ
- ጽህፈት መሣሪያ ምድብ
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ምድብ
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ምድብ
- የህትመት ስራዎች ምድብ
- የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ምድብ
- የስፖርት ትጥቅ ምድብ
- የጽዳት ዕቃ በጨረታ ለመግዛት ማወዳደር ይፈልጋል::
ስለዚህ በጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁTir /ቲን ናምበር/ ያላቸው ለመሆናቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቸና ማረሚያ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁTir 9 በስራ ሰዓት የማይመለስ 100 ብር በእያንዳንዱ ምድብ/ሎቶች/ ገዝተው መውሰድ የሚችሉ ፣
- ግዥው ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ምድብ ውስጥ በተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- አሸናፊው ጨረታውን ማሸነፉ ሲገለፅለት 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁTir 9 ለዚሁ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ከሆኑ የስራ ልምድ የብቃት ማረጋገጫ በየደረጃው ከሚገኙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዝ ልማት ኤጀንሲዎች እውቅና የተሰጣቸው ለመሆኑ ማቅረብ የሚችሉ፣ ልዩ አስተያየት በተመለከተ መመሪያው በሚፈቅድላቸው መስተናገድ የሚችሉ
- ጽ/ቤቱ ከሚገዛቸው ዕቃዎች ላይ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው::
- በሚወዳደሩበት ወቅት ዋጋ በሞሉበት ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅታቸውን ማህተም ማሳረፍ አለባቸው::
- የጨረታ አሸናፊዎች ውጤት በተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል ይዘው ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ማረሚያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታዩ ቀናት በ16ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ቢሮ ቁTir 9 ይከፈታል፤ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል::
- የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ግ/ፋ/ን/ብ/አስ/ደ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁTir 9 ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁTir 058 665 11 49 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
የብቸና ማረሚያ ቤት