የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጽህፈት መሣሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች
ግዥ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 003/2013
በብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን አቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዱስትሪ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሣሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች በግዥ እንዲቀርብለት ይፈልጋል፡፡
- የጽህፈት መሣሪያዎች
- የጽዳት ዕቃዎች
ስለሆነም ከላይ በሰንጠረዥ የተገለፁት ዕቃዎች ዝርዝር ስፔስፊኬሽን፣ አይነትና ብዛት የያዘ ከአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ ግዥ፣ አስተዳደር በሎት ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 41 ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይቻላል፤
በዚሁ መሠረት ተጫራቹ በራሱ ትራንስፖርት ኢንዱስትሪያችን ቅጥር ግቢ የሚገኘው ዋናው ስቶር ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ሲሆን የመሸጫ ዋጋና የማቅረቢያ ጊዜን በመግለፅ የጠቅላላ ዋጋውን 2% የጨረታ ማስከረቢያ CPO ማቅረብ የሚችል፣ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ሰርተፍኬት ኮፒ፣ የቫት ሰርተፊኬትኮፒ፣ የቲን ነምበር ሰርተፊኬት ኮፒ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ እንዲሁም ቲከኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ ሆኖ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ አሽጐ ዋናውና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ኣየር ላይ የሚቆይ ሆኖ ልክ በአስራ አምስተኛው ቀን የኢንዱስትሪያችን ግዥ አስተዳደር ዋና ቢሮ ቁጥር 41 ድረስ በመቅረብ እንድታስረክቡ እየጠየቅን በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው መዝጊያ ሰዓት ሲሆን በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እየገለፅን በተጨማሪም ተጫራቾች ያቀረቡትን ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በመወዳደሪያ መግለፅ ያለባቸው ሆኖ ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት ቀን በኋላ ላሉት 28 ቀናት ዋስትናው ህጋዊነት፣ የሚረጋግጥ መሆን ይኖርበታል፡፡
ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ከአ/አ ወደ ደ/ዘይት መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ገላን ከተማ
ሳይደርስ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ ከASTCO
FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፡– ስልክ ቁጥር 0114340409/0114350608
ሞባይል ቁጥር 0911451141/0923801915
በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ