የጨረታ ማስታወቂያ
መሥሪያ ቤታችን ለ2013 በጀት ዓመት 2ተኛ ዙር የተሽከርካሪ ዕቃ መለዋወጫዎች፣ጎማዎችና ባትሪዎች እንዲሁም የውጭ ጥገና የማሽን ሾፕ፣ የፖምፖ፣ የመኪና እጥበት፣ የራዲያተር፣ የጭስ ማውጫ፣ የጎማ ባላንስ፣ የዲያጎነሲስና የመኪና መብራት እጥበት ሥራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸውና የ2013 ዓ.ም ግብር የከፈሉ እንዲሁም በመንግስት ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውንና ጨረታ ለመካፈል የተፈቀደላቸው መሆኑን የሚገልጽ ክሊራንስ ቀኑ ከጨረታ መክፈቻ በፊት የወጣ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቀበና ሼል ወረድ ብሎ አደባባዩ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮአችን ቀርበው የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ (CPO) ከጨረታው መክፈቻ ዕለት አስቀድሞ ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በተገለፀው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ፡–
- የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም
- የውጭ ጥገና የማሽን ሾፕሥራዎች ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። በዚሁ ዕለት የጨረታው ተሣታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ናሙናዎችን ከተከፈተበት ቀን ማግስት ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት በ10 ቀን ጊዜ ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡0111-23-84-88፣ 0111-23-98-24፣ 0111-23-84-64 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት
የሎጅስቲክስና ኮንስትራክሽን ዋና መምሪያ