ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
ማኦ/ኮ/005/2013 ዓ.ም
- የጨረታው ዓይነት– የመንገድ ሥራ ማሽን ኪራይ
- የተጠቃሚ ሀገር ሥም–ኢትዮጵያ
- የክልሉ ሥም ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት
- የወረዳው ሥም ማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ገጠር መንገድ ዴስከ
- የፕሮጀክቱ ሥም – የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ ልማት ፕሮጀክት
- የሥራ ቦታዎች-3 ቀበሌዎች /ቦሶስ፣ ኬሰርና ዋንጋ/
- የሥራ ብዛት– 16 ኪ.ሜ
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ገጠር መንገድ ዴስክ በዲ.አር.ዲ.ፒ ኘሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በወረዳው ውስጥ በሚገኙ 3 ቀበሌዎች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታ እና በመንገድ ሥራ ላይ ለማሰማራት ማሽኖችን ማለትም
- ዶዘር ብዛት 1፣
- ግሬደር ብዛት 1፣
- ሩሎ ብዛት 1፣
- ገልባጭ መኪና ብዛት 4፣
- ባለጎማ እስካቫተር 1፣
- ባለሠንሠለት እስካቫተር ብዛት 1 እና የውሃ ቦቴ ብዛት 1 ለመከራየት
በወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ማኦ/ኮ/005/2013 ዓ.ም መሠረት የአንዱን ማሽን ዋጋ በሰዓት እንዲያሳውቁን በማለት ለ30 ቀናት የሚቆይ ብሄራዊ የሆነ ግልጽ ጨረታ አሳውጇል፡፡ በመሆኑም፤
የማሽን ብዛት በቁጥር |
የማሽን ዓይነት |
የ1 ማሽን የሰዓት ፍጆታ በቀበሌው |
የቀበሌው ሥራ በእቅድ በኪ.ሜ |
1 |
ዶዘር |
400 |
16 |
1 |
ግሬደር |
450 |
|
1 |
ሩሎ |
450 |
|
1 |
ባላ ጎማ ኤክስካቬተር |
350 |
|
1 |
ባለ ሠንሠለት ኤክስካቬተር |
350 |
|
1 |
የውሃ ቦቴ /ሻወር ትራከ |
400 |
|
4 |
ዳምፕ ትራከ |
በሥሩ ዝርዝሩ |
የቀበሌው ሥም |
የ2013 በጀት ዓመት እቅድ |
መለኪያ |
ብዛት መጠን |
የቀበሌያቶች ከወረዳ ማዕከል /ቶንጎ/ ርቀት በኪሜ |
ቦቦስ እሽቃባ |
መንገድ ግንባታ |
በኪሜ |
7 |
16 |
ከሴር መ1/2 |
መንገድ ግንባታ |
በኪሜ |
4 |
24 |
በመሆኑም፤
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በ2013 በጀት ዓመት ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጥሩ ሥነ ምግባር ባለቤትና ከነበሩበት ቦታ ማሽኑ ሌላ ሥራ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ የተረካከቡበት ምስክር ወረቀት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- የሚያከራዩን መሣሪያዎች የራሳቸው ለመሆኑ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ወይም አግባብ ባለው ሙሉ የህግ ውከልና ማቅረብ የሚችሉ ዶዘር፣ ግሬደር፣ ሮሎ፣ እክስካቫተር እና የውሃ ቦቴው የተመረተበት ዘመን ከ2015 በኋላ የሆነ የገልባጭ መኪናዳምፕ–ትራክ) 2015 በኋላ የሆነ።
- የድርጅታቸውን (የቢሮቸውን) አድራሻ ማሳየት የሚችሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በይፉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር በማድረግ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት አሶሳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ30 ቀናት (ሰላሳ ቀናት) በአየር ላይ የሚውል ሲሆን፤ በ31ኛው(በሰላሳ አንደኛው ቀን) ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም /ለመገኘት ባይችሉ እንኳን የመሥ/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ ጨረታውን ከመክፈት አያስቀረውም፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ህዝባዊ በዓላቶች እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት አሶሳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ውስጥ ተዘጋጅቶ በተቀመጠው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የሚያከራዩትን ማሽኖች የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር (ሊብሬ) ኦርጅናልና ኮፒውን እና በውልና ማስረጃ የውክልና ደብዳቤ ይዘው ካልቀረቡ የጨረታ ሰነድ አይሸጥላቸውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲያቀርቡ ለቴክኒካል 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ ሲሆን ለፋይናንሻል ደግሞ 1 ኦሪጅናልና 2 ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት።
- የጨረታ ሰነድ በሚገዙበት ወቅት የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር(ሊብሬ) አሳይተው ካስመዘገቡት ማሽን ውጭ ጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው ቢያቀርቡ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለሁሉም ማሽኖች በጠቅላላ 120,000 /አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማሸኑን በቶንጎ ከተማ ድረስ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ዘወትር በሥራ ሰዓት የወረዳ ግዥ ባለሞያ የሆኑት ጋር በስልክ ቁጥር 09233881/0980248864 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ
የስደተኞች ተፅዕኖ ምሳሽ ልማት ፕሮጀክት
አሶሳ