የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በቤ/ጉ/ክ/መንግስት በመተከል ዞን የማንቡከ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ለማስተማሪያና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- የህንፃ መሣሪያ፣
- የእንጨት ውጤቶችን፣
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
- ጽህፈት ማሣሪዎችን፣
- የኮምፒውተር መለዋወጫዎችን፣
- የጽዳት ዕቃዎችን፣
- የቧንቧ ውሃ ዝርጋታ ዕቃዎችን፣
- ብረታ ብረታ፣
- የመኪና መለዋወጫዎችን፣
- ህትመት፣
- የደንብ ልብስ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሣተፍ ትችላሳችሁ።
- የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው።
- የዘመኑን ግብር የከፈለ።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው።
- የግዥ መጠን ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ድርጅቱ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ/ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የማንቡከ ቴ/ሙ/ት/ስኮሌጅ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል።
- ጨረታው የሚሞላው በነጣላ ዋጋ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 ብር በመክፈል አመራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት/ኢ/ል/ት/ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 226 ቀርበው ማግኘት ይችላሉ።
- የአሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በቅርንጫፍ በር ድረስ ማስረከብ ይኖርበታል። እንደ አስፈላጊነቱ የባለሙያ እገዛ የሚያስፈልጉ ዕቃዎች በባለሙያ እየተፈተሹ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል።
- በፖስታውና በሰነዱ ላይ ህጋዊ ማህተምና ፊርማ መኖር አለበት።
ማሣሠቢያ፡-
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውላሉ።
- በ16ኛው ቀን በ 13/5/2013 – ከ2፡30-5፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርብዎታል።
- የጨረታው መቆያ ጊዜ ከ28/4/2013 እስከ 12/5/2013 ዓ.ም ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ቢሮአችን በቀን 23/5/03 ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 5፡30 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል።
- ጨረታውን ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሲፒኦ መቆያ ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ በውል ላይ ይገለፃል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው
- በዚህ ጨረታ ላይ ሳይካተቱ የቀሩ ዝርዝሮች በመንግስት ግዥ ደንብና መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
- ጥሬ ገንዘብ በፖስታው ውስጥ ማስገባት አይቻልም። በጥሬ ገንዘብ ከሆነም በደረሠኝ በእጅ መስጠት ይቻላሉ።
- ዝርዝር መግለጫ ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን በመደወል ወይም ቅርንጫፍ ቢሮአችን አማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት/ገ/ኢ/ል/ት/ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 226 ድረስ በመምጣት ማግኘት ይችላሉ።
- ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁ. 09 17 18 18 54/09 17 1839 07/ 058 263 01 45
በቤ/ጉ/ክ/መንግሥት በመተከል ዞን
የማንቡክ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ