የቢሮ ግንባታ ግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ
በቤንች ሸኮ ዞን በጊዲ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2012 ካፒታል በጀት ዓመት በወረዳው የቢሮ ግንባታ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈረቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ በግንባታ ፍቃድ ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የሆኑት ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TUN ነምበር ያለውና የቫት ተመዝጋቢነትና የግንባታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሚያስገቡበት ወቅት የፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በተለያዩ (ሦስት) ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ በማሸግ አድራሻቸውን በትክክል ሕጋዊ ማህተም በማሳረፍና የስልክ ቁጥራቸውን በመጻፍ ከዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) የኢት/ያ ብር በደ/ከ/ለቤንች ሸኮ ዞን በጊዲ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም ከማንኛውም ከሕጋዊ ባንክ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ከ2፡30 ሰዓት እስከ 1፡30 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ክፍያውን በጊ/ቤ/ወ/ገቢቅ/ባለስልጣን ጽ/ቤት የማይመለስ ኢት/ያ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ሕጋዊ ደረሰኝ በመያዝ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በማንኛውም ቦታ በሥራ ሂደት ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ያልደረሰው ተጫራች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ የሚከፈትበት ዕለት በዓል ወይም ካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ስ/ቁ፡ 0478907444
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ቤንች ሽኮ
ዞን የጊዲ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ ል/ጽ/ቤት