ቀሪ ሥራዎች ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ በባስኬቶ ልዩ ወረዳ የባስኬት ልማት ማህበር የተጠቃሚውን ፍላጎት ለማርካትና የራሱን የውስጥ ገቢ አቅም ለማሳደግ ያስችል ዘንድ በልዩ ወረዳ ርዕሰ ከተማ ላስካ ከዚህ በፊት G+1 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሥራ ማስጀመሩ ግልጽ ሲሆን የተጀመረው ግንባታ አልተጠናቀቀም፡፡ ያልተሠሩ ቀሪ ፔንስዮን ሥራዎችን ቀጥሎ ባለው መስፈርት አማካይነት በግልጽ ጨረታ ሂደት ህጋዊ ኮንትራክተሮችን አወዳድሮ በመለየት ቀሪ ማስጨረሻ ሥራዎችን በ2013 ዓ/ም በበጀት ዘመኑ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በግንባታ ዘርፍ ፍቃድ ደረጃ BC/GC ሆኖ ከደረጃ 4 እስከ 6 ተቋራጭ የሆነ/ች
- የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ገላጭ መረጃ ያለው/ላት
- የዓመቱን የሥራ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/ች
- በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገበች
- ከጠቅላላ ክፍያ TOT 2% ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ/ች
- ተወዳዳሪው የቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንቱን በሰም የታሸገ ፖስታ ለእያንዳንዱ አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ በመጨረሻም በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተወዳዳሪዎች በቴክኒካል ውጤት 70% እና ከዚያ በላይ ማምጣት ሲቻል ለፋይናንሻል ውድድር ማለፍ የሚችል መሆኑን ማወቅ አለበት::
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር CPO or unconditional Bank Grant ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ CPO or unconditional Bank Grant በቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በአካባቢው ለቤቱ ግንባታ የሚያስፈልገውን ማሽነሪ ሙሉ ግብዓት በራሱ ማቅረብ የሚችል ማለትም፡- ገልባጭ መኪና ስለመኖሩ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ሚከሰር ያለው፣ ኤልክትርካልና ሲቪል የሳይት መሀንዲስ ያለው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከታኅሣሥ 14/4/2013 ዓ.ም እስከ 4/5/2013 ዓ.ም በተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዶክመንቱን እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት በላስካ ከተማ ከባስኬት ልማት ማህበር ጽ/ቤት በመግዛት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ዶከመንት ሳጥን በ05/5/203 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች /ህጋዊ ተወካዮቻቸው እና የጨረታ ኮሚቴ አባላት ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ከተወዳዳሪዎች መካከል የውሸት ማስረጃ ያቀረበ ወይም ለማቅረብ የሞከረ ተጫራች ከውድድሩ ይሰረዛል፡፡
- መ/ቤቱ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር-046 240 0317/0910610378/0955420618
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ባስኬት ልማት ማህበር ጽ/ቤት
ላስካ