ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በፋሲሎ ክ/ከ/አስ/ጽ/ቤት የ2013 በጀት አመት አገልግሎት የሚሰጡ
- ሎት 1 የስቴሽነሪ /የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ሎት 4 ብትን ጨርቅ፣ የተዘጋጁ ልብሶች እና ጫማ፣
- ሎት 5 የህንጻ መሣሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
- በስሙ የታተመ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ
- ጨረታው ዋጋው ብር 200 ሺህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከአንድ እስከ አራት የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ፋ/ክ/ከ/አስ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በብር /አስር/ 10 በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢን ቦርድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይንም በሁኔታ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ፋሲሎ ክፍለ ከተማ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የሚቀርቡ ዕቃዎች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁና ናሙና ለቀረበለት ዕቃ በምናቀርበው ናሙና መሰረት መሆን አለባቸው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በየምድቡ በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ዋጋ ይሆናል፡፡
- ይህ ጨረታ በአየር ላይ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ /እንቨሎፕ/ ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች ፋ/ክ/ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-222-15-66 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-222-15-66 ላይ ይደውሉ ጽ/ቤቱ
በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፋሲሎ ክ/ከ/አስ/ጽ/ቤት