ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በባሌ ዞን የጎባ ከተማ ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት የ 2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግዥ በከተማው ላሉ መ/ቤቶች የሚያገለግሉ
- የትምህርት መሳሪያዎችን፤
- የማሽኖች ስፔርፓርት ፣
- Energy Saver (Wood Saving Stove;
- hand Washing Material (Facility out touching;
- back Knapsack spray)እና
- ሻይ ቡና የቢሮ እቃዎች
- የተለያዩ የከተማ ማስዋብያ ችግኞች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በማንኛውም በዘርፉ አገልግሎት ሰጪ የተሰማሩ በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቲን ነምበር /Tin No/ ተመዝጋቢ መሆናችሁን የዘመኑን ግብር የከፈላችሁበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፣፡
- ከላይ የተጠቀሱትን የውድድር ዓይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ/CPO/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ከጎባ ከተማ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 6:30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት ብቻ 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Acc.No 1000028126712 በማስገባት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በኤንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በማድረግ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚያው ዕለት በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች የማጓጓዢያ ማስጫኛና ማውረጃ ወጭውን በመቻል ጎባ ከተማ /ኢ/ት/ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- የዕቃዎቹን ዋጋ መ/ቤቱ የሚከፍለው ንብረቱ ሙሉ በሙሉ ንብረት ክፍል ገቢ ሆኖ በጥያቄው መሠረት መቅረቡ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ጨረታውን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸዉ ከ5 ቀን በኋላ በመስሪያ ቤቱ ቀርበው ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል በተጨማሪም ውል ከገቡ በኋላ በ15 ቀን ዕቃውን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ዕቃዎቹ ገቢ ሆነው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ለአላቂ ዕቃዎች የ1 ወር ለቋሚ ዕቃዎች የ1 ዓመት ጊዜ ጋራንት/ዋስትና መስጠት የሚችልና ዕቃዎቹ የተበላሹና ኦርጅናል ካልሆኑ ለመመለስ ግዴታ የሚገባ መሆን አለባት፡፡ እንዲሁም ናሙና ማቅረብ የሚችል ሲሆን ሠነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) በኢትዮጵያ /ንግድ ባንክ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ / ብቻ በጎባ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ አቅራቢዎች የውል ማስከበሪያ የዕቃውን ሙሉ ዋጋ 10%(አስር ፐርሰንት) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከሠነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስምና /Brand Name / መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ጎባ ከተማ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0226612764 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በባሌ ዞን የጎባ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት