ግልጽ የጨረታ ማስታቂያ
በባሌ ዞን የዲንሾ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ማለትም፡ –
- የጽህፈት መሳሪያዎችን፣
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣
- አላቂ የፅዳት እቃዎች እና የንፅህና መስጫ ቁሳቁሶችን ፣
- የተማሪዎች ካርድ፦ ቾክ
- የተለያዩ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣
- ምንጣፍ፣
- የመኪና ጎማ እና
- የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታ ለመሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
- አዲስ ንግድ ፍቃድ ወይም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው) እና የ2012 ዓ.ም ግብር ገብሮ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው
- የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 100.00/ መቶ ብር/ የማይመለስ በመከፈል እስከ 15የስራ ቀናት ድረስ መ/ ቤታችን ግዥ እና ፋይናንስ ጽ/ቤት ቀርቦ መግዛት የሚችል
- የጨረታ ሰነድ ሲያስገቡ ኦርጅናል እና ኮፒ ለተለያዩ ፖሰታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 5000.00 /አምስት ሺ ብር / በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለበት
- የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 23/2/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ፡ እስከ 3:59(ሶስት ሰዓት ከሀምሳ ዘጠኝ ደቂቃ ማስገባት አለበት 4:00( አራት ሰዓት ) ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30(አራት ሰዓት ከሰላሳ)ላይ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በይፋ ይከፈታል
- በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ ያለው ተጫራች ጨረታው ከተከፈበት ቀን አንስቶ እስከ 5/አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በጽሑፍ ካላስገባ ቅሬታው ተሰሚነት አይኖረውም፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል የሚፈርምና የውል ማስከበሪያ 10% ማቅረብ የሚችል::
- አሸናፊው ውል ከፈጸመበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ እቃዎችን ዲንሾ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል::
- የማጓጓዣ ሂሳብ በተጫራቹ፡ የሚሸፈን ይሆናል::
- መስሪያ ቤቱ፡ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብት አለው።
- አሸናፊዎች ያሸነፉትን የዕቃ ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
በተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር: 0221 191 223 /0913528042
በባሌ ዞን የዲንሾ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት