ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በቢሾፍቱ ሆስፒታል ለ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሆን ህትመት ሥራዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ እና የሙያ ፈቃድ ያለው፣የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የቫት ከፋይ የሆነ
- በህትመት ሥራ ዘርፍ የሥራ ፈቃድ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገብ ማስረጃ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይና የቲን Tin Number ያለው::
- የጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ በህትመት ሥራ ዘርፍ በኦሮሚያ ክልል ስር የተደራጀ እና ከጥቃቅንናአነስተኛ ተቋማት ከ2012 የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናትና ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሆስፒታሉ ከቢሮ ቁጥር 47 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ ብር) በሆስፒታሉ ስም ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች ከእያንዳንዱ በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ካቀረቡ የሚያልፉ መሆኑን፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት በሚታሽግበት ፖስታ ወይም ኤንቨሎፕ በሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ በኃላፊው ስምና ፊርማ ማህተም ያለው መሆን አለበት፡፡ እስከ አስረኛው የሥራ ቀን ድረስ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4/1/2013 ቀን ልከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በሆስፒታሉ ላይብረሪ ይከፈታል፡፡
- በውድድሩ አሽናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ማሽነፋቸው ከተገለፀበት እና ከ5 የቅሬታ ቀ በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ውል ፈፅመው በአንድ ወር ውስጥ የህትመት ሥራውን ያስረክባሉ፡፡
- ሆስፒታሉ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡0114371271/ 0114338187 መደወል ይችላሉ።
በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የቢሾፍቱ አጠቃላይ ሆስፒታል