የጨረታ ማስታወቂያ
በቡኖ በደሌ ዞን የቦረቻ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልላዊ የመንግሥት ግዢ አዋጅ ቁጥር 157/2002 ዓ.ም መሰረት
- የተለያዩ ብትን ጨርቃ ጨርቆችና የተዘጋጁ የደንብ አልባሳት
- ስቴሽነሪና አላቂ የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች
- ቋሚ የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች/ፈርኒቸር/
- የተለያዩ የመኪናና የሞተር ሳይክል ጎማና ካላማዳሪያ
- የተለያዩ የህትመት ስራዎች
- የተለያዩ የሞተር ሳይክሎች
- የተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ለዚሁም የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- ከላይ በተዘረዘሩ የግዥ አይነቶች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያደሱ
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000/አምስት ሺህ/ ብር በሲፒኦ ወይም በካሽ ማስያዝ የሚችሉ
- VAT NO እና TIN NO ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ
- በኣቅራቢነት ዝርዝር መዝገብ ላይ መመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ
- ናሙና ማቅረብ የሚችሉ
- ተወዳድሮ ያሸነፈውን ዕቃ ሁሉ እስከ ቦረቻ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ
- የተጠቀሱትን ዕቃዎች ሁሉ ኦርጂናል የሆኑ ዕቃዎች ማቅረብ የሚችልና ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ነጋዴይህ ማስታወቂያ ወጥቶ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት መሀከል ቦረቻ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በማንኛውም የመንግሥት የስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ዕቃ እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤምቨሎፕ በፖስታ አድርገው ቦረቻ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በማምጣት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ ፡
- ይህ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ የሚሸጥ በብር 100.00/100/መቶ ብር/የማይመለስ የሚሸጥና በዚሁ በተጠቀሰው ቀን መሀል ተሞልቶ የሚመለስ መሆኑን እየገለፅን በ16ኛ/አስራ ስድስተኛ የስራ ቀን ላይ በቦረቻ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1/አንድ/ ውስጥ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3:30 ላይ ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን::
- በቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ማቅረብ አይቻልም።
- ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች በተራ ቁጥር 2.3.4.5.6.7 እና 8 ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ትከክለኛ ማስረጃ ስለመሆኑ የሚገልጽ ኦርጂናልና ኮፒው በአንድ ፖስታ ታሽጎ መገኘት አለበት፡፡ ካልሆነም ኮፒው ከኦሪጅናሉ ጋር አንድ ስለመሆኑ የሚገልጽ በኮፒው ላይ የድርጅቱ ማህተም በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን፡፡
- የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- እንዲሁም ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች መካካል አንዱ እንኳን ቢጎድል ፖስታው ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በውስጡ የሌለውን ማስረጃ አቀርባለው ወይም በእጄ ይዣለሁ የሚል ሰበብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ በቂ ምክንያት ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0477800024 ወይም 0477800201 ደውለው መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በቡኖ በደሌ ዞን የቦረቻ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት