ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2013
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች ላይ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃዎችንና አገልግሎት ግዥዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 2 የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 3 የመኪና ጎማ ጌጣጌጥና ታፕሴሪ
- ሎት 4 የኮምፒውተር የፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ጥገና
- ሎት 5 የሳውንድ ሲስተምና የዲኮር አገልግሎት ግዥ
- ሎት 6 የመኪና ጥገና/ጋራጅ
በመሆኑም ተጫራቾች፡
- በዘርፉ ህጋዊና በጀት ዓመቱ የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /tin no/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ያላቸው::
- ተጫራቾች ከግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- ለሚወዳደሩባቸው የዕቃ/የአገልግሎት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ለሁሉም ሎቶች በመወዳደሪያ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን ዋጋ በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል 1 ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ፣ 1 ፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናል እና የፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም 1 ሲፒኦ ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- ፋይናንሻያል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ኦርጅናል በአንድ ኤንቨሎፕ ያቀረበ ተወዳዳሪ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ላይ በሚገኘው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት
የቂርቆስ ክ/ከ/አስ/ አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ
ስልክ 0115548264
በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት