ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ የፈለገዮርዳኖስ አፀደ ሕፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት የ2013ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን በግልፅ ጨረታ ወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- አላቂ የትምህርት እቃዎች
- አላቂ የፅዳት እቃዎች
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ
- የህክምና እቃዎች
- ለሕንፃና ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚ እድሳት እና ጥገና
- ቋሚ እቃ
- ለፕላንትና ማሽነሪ እድሳት ጥገና
- አላቂ የቢሮ እቃ
በዚህ መሰረት በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ፡
- በዘርፉ የተሰማሩ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑ ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /cpo/ 3,000.00 (ሶስት ሺ ብርብቻ ማቅረብ የሚችል
- . ለጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ 50.00 (ሀምሳ ብር ብቻ) የማይመለስ ስመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀንጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በፈለገዮርዳኖስ አፀደ ሕፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 30 የግንባር በመቅረብ መግዛት ይቻላል
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው
- የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በታሸገ ኢንቨሎፕ በተለያየ ፖስታ አሽገው ሲመጡ /cpo/ ደግሞጨረታው ኮፒ ባለበት ፖስታ ውስጥ በማስገባት አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋዝርዝር ሰነድ ላይዋጋው ማቅረቢያ በግልፅ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበትዕለት ጀምሮ እስከ 10 የሥራ ቀና ድረስ ለዚሁ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያው ከወጣበት 11ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰአት በት/ቤቱ ቅጥር ግቢፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁ. 30 ይከፈታል፡ ፡የ11ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰአትይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊው ለውል ማስከበሪያ የሚሆን ያሸነፈበት እቃ የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና በባንክ በተረጋገጠየክፍያ ማዘዣ /cpo/ ማስያዝ አለበት፤
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የነሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
አድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ፈለገ ዮርዳኖስ አፀደ ሕፃናትናየመ/ደ/ት/ቤት
ስልክ ቁጥር 0114701490/0114164270/0114161936
በቂርቆስ ክ/ከተማ የፈለገዮርዳኖስ አፀደ ሕፃናትናየመ/ደ/ት/ቤት