የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2012
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ለ2012 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ግዢ ደረጃቸውን የጠበቁ
- የቋሚ ዕቃ እንዲሁም ፕሪንተር ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፦
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ በ/ኢ/ትብብር ሚኒስቴር ወይም በኣዲስ ኣበባ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር/supplier list/ ውስጥ የተመዘገበበትን የምስክር ወረቀትና ማንኛውም ተወዳዳሪ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ኦርጂናልና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም ::
- ተጫራቾች ጨረታው ማስታወቂያ ላይ በተዘረዘሩት ዕቃ ዓይነቶች በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸው አድራሻቸውና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ መመሪያና ሰነድ ላይ በመፈረም በማህተም ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነቶች ለይተው መፃፍ አለባቸው::
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ድርጅት ዕቃዎችን ከወረዳ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጋር ውል በገባ በአስር (10) ቀናት ውስጥ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ወይም ወጪ ማስረከብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 5,000 (አምስት ሺ ብር ) ማስያዝና ኮፒ ለተደረገው የጨረታ ሰነድ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ያሸነፈው አካል ማሸነፉ በጽሑፍ እንደተገለጸለት ከመስሪያ ቤቱ ጋር በ7 (ሰባት ) ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት፡፡
- በጨረታው ያሸነፈው ድርጅት ከጽ/ቤቱ ጋር ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ተመላሽ አይሆንም::
- በጨረታው ተወዳድሮ ያሸነፈ አቅራቢ ውል ሲፈጽም የግዢው አጠቃላይ ዋጋ 10 % ውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል፡፡ 11ኛ ቀን በዓል ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር-011-416-08-37/0911460014/ 0924780233/0911460014 በመደወል ወይም ከደንበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ ድሪምላይነር ሆቴል ወረድ ብሎ በቀድሞ ቀበሌ 35 በአሁኑ ወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት መጠየቅ ይቻላል፡፡
በቂርቆስ /ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት