የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምስ/ጎህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት
- የሚውሉ ቋሚ ዕቃ፣
- የጽሕፈት መሣሪያ፤
- የደንብ ልብስ እና
- የጽዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በዚህ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግሥት ንብረት ግዥ አስተዳደር ኤጀንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅብዎታል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ጨረታ ማስከበሪያ አምስት ሺህ ብር (5000) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጥራትና ማስረጃውን የጠበቀና ለዚህም ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በት/ቤቱ ክ/ሂ/ግ/ን/አስ/ጠ/አገ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የሥራ ቀናት ዘወትር የሥራ ሰዓት ት/ቤቱ በከ/ሂ/ግ/ን/ኣስ/ጠ/አገ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች (ሕጋዊ) ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት በት/ቤቱ በክ/ሂ/ግ/ን/አስ/ጠ/አገ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ካዛንችስ ቶታል ፊት ለፊት አዋሬ መንገድ ምስ/ጎህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ስልክ ቁጥር፡– 0115-15-56-52
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ
በቂርቆስ ክ/ከተማ ምስ/ጎህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት