የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ በጋሞ ዞን በቁጭ አልፋ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2013ዓ.ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ማቴሪያሎችንና ሥራዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው የሚፈልጋቸውማቴሪያሎች
- የሕንፃ መሣሪያዎች
- የጽህፈት መሣሪያዎች
- የሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- የሠራተኞች ደንብ ልብስ
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
- የባጃጅ ሞተር ሳይክል
- ጀነሬተር
- መንገድ ግንባታና የአፈር ሥራ
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ በመንግስት ግዥ አዋጅና ደንብ መመሪያ መሠረት፡-
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የተከፈለበት መረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር TIn Number ያላቸው፣
- ቫት ተመዝጋቢ የሆነ መረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፣
- ከሽያጭ ዋጋ ላይ የመንግስት ግብር 2% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የጨረታው ሁኔታ በአይተም/በጥቅልል/ ሊሆን ይችላል፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት/ኦርጅናሉን በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በቁጫ አልፋ /ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ-3 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝር የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /ኣንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቁጫ አልፋ /ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ 2.5% ከጠቅላላ ዋጋ በባንክ የተረጋገጠ CPO/በጥሬ/በቼክ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው የጨረታው ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል፣
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፣
- በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃውን እስከ ቁጫ አልፋ /ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ የጫኚ የአውራጅና የጭነት ወጪን በመሸፈን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም የተጫራቹ ወኪል ያለመገኘት ጨረታውን መክፈትን አያስተጓጉልም።
- 16ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ማሳሰቢያ፡ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 091687 69 46/0916108292/0984666189 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ በጋሞ ዞን በቁጫ
አልፋ ወረዳ ፋይናንስ /ጽ/ቤት